Sunday, December 26, 2010

History is the self-consciousness of humanity,,,,,,,. Droyson

የእድገት በሕብረት የእውቀትና የስራ ዘመቻ
ያትውልድ፤ ከታሪካችን
ከሳᎀኤል ሽፈራው/ዳላስ

ለፍቅር፣ ለብልጽግና፣ ለጸጋና ለእድገት ቀናኢ የሆነ ትውልድ በአገራችን ተነሳ። ያባቶቹን የማይጮ፣ የሽሬ፣ የኤሊባቡር፣ የጎሬ፣ የብቸና፣ የመላ ጎጃም፣ የሜጫ፣ የሸዋና የመላ ጎንደር አርበኝነትን ገድል ካባቶቹ ሲሰማ ያደገው ትውልድ፤ በመንፈስም በስጋም ከነሱ የወሰደውን የጀግንነት ታሪክ በእድገት ለመለወጥ መነሳሳቱ ነበር በኋላ ለዘግናኝ ፍጅት ያውም በወገን እጅ የደረሰበት። የዛሬ ሰላሳ አምስት አመት ታሕሳስ አጋማሽ የእድገት በሕብረት የእውቀትና የትምህርት ዘመቻ ታውጆ በጥር ሁለት ቀን 1967 እ.ኢ.አ የመጀመሪያወቹ ወጣት ተማሪወች ዘመቱ። ለ13 አመታት የታገሉለት የመሬት ላራሹ ሕልምና ሳይማር ያስተማራቸውን አርሷደር ለመቀላቀር የዘመቻ መዝሙራቸውን እያቀነቀኑ ተጓዙ

በእድገት በሕብረት እንዝመት
ወንድና ሴት ሳንል ባንድነት

ዘመቻው አንድ ፊደል የቆጠረ ትውልድን ይዞ የተጓዘ ታሪካዊ ኩነት ነበር። ወጣቶቹ ከቤተሰብ ተለያይተው ወደገጠሪቷ ኢትዮጵያ ሲጓዙ በሀዘን ሳይሆን በደስታና በመንፈሰ ሙሉነት ነበር። አባቶቻቸው በ1928 ዓም ከወራሪ ጠላት ጋር ሲፋለሙ። ገሚሶቹም በአገሪቱ ዱር ገደል እንቢ ለነጻነቴ ብለው በመዋደቃቸው ኢትዮጵያ የተባለችን የጥቁር አገር ክብሯን ዳግም ለመጠበቅ ችለዋል። ታሪካዊውን የአውሮፓ ወራሪ ጠላት ዳግም አሳፍረው መልሰዋል። ይህን በስነ ልቦናቸው ያልለዩት የየካቲት ወጣቶች። የገጠሪቷን ኢትዮጵያ ኑሮ ለመኖር በጉጉት እንጅ በሐዘንና በትካዜ አልነበረም የተጓዙት።

ያትውልድ የምንለው የየካቲቱ ለውጥ ፈላጊ ትውልድ የእድገት በህብረት ዘመቻን በሁለት መንፈስ ነው የተቀበለው። በአንድ በኩል ለዘመናት የተጋደሉለትን የዴሞክራሲና የሕዝባዊ መንግስት ጥያቄ በወታደራዊ መንግስት መነጠቅና ከተማውን ለቀው ቢወጡ ይህ ስልጣኑን ለማደላደል ከወዲያ ወድህ የሚወራጨው ደርግ ጠቅሎ ሊይዝና ምኞታቸውን ሊያደበዝዝ መሆኑ ሲሆን። በሌላ በኩል ለዘመናት የዘመሩለትና የታገሉለት አፈር ገፊውን መቀላቀሉ ለነገ የማይባል አጋጣሚ ሆኖ በመገኘቱ ነው። በዚህ ሁለት አስቸጋሪ ጉዳዮች የተያዘው ወጣት ሆነም ቀረ ዘመቻውን ወደመቀበሉ አመራ። በጥር ሁለት የጀመረው ዘመቻ እስከ ሐምሌ ቀጠለ። 90% የሚሆነው ዘማችም ወደየምድብ ጣቢያው ሔደ።

በየካቲት 25 1967 ዓም አዲሱ የመሬት ላራሹ አዋጅ ወጣ። ምንም እንኳን የተሟላ ባይሆንም፡ ይህን አዋጅ በስራ እንዲተረጎም ያደረገው በዚሁ የእደገት በሕብረት ዘመቻ ላይ የነበረው ወጣት ነበር።

በዚህ አጋጣሚ ስለመሬት ለአራሹ ይሁን ብለው ሰላማዊ ሰልፍ የወጡ ወጣቶች በአገሪቱ የነበረውን የመሬት ስሪት በቅጡ የማያውቁት ብዙወች ነበሩ። ከሰሜን ክፍለ ሀገራት መሬት በእርስት የተያዘበት አካባቢ ተወልደው ያደጉ ሲሆኑ፤ የደቡብ ኢትዮጵያን የጉልተኝነት የመሬት ስሪት አያውቁም። እንዲሁ በደቡብ ኢትዮጵያ ተወልደው ያደጉ ወጣቶች ወደሰሜን ሲዘምቱ እነሱ ተወልደው ካደጉበት የጉልተኝነት ስሪት የተለየ መሆኑ ለነሱም አዲስ ነገገር ነበር። በዚህም ይሁን በዚያ የዚያ የለውጥ ፈላጊ ትውልድ ወጣቶች በአንድና ለአንድ የታገሉ በመሆናቸው ሕዝባቸው የተሻለ ስርአት እንደሚፈልግ፣ ለውጥም መምጣት እንዳለበት በሁሉም የታመነበት ነበር።

ወጣቶቹ ዘመቻ ጣቢያወች ከደረሱ በኋላ፤ ትግሉ መንታ ሆኖ ጠበቃቸው። አንደኛው የገበሬ ማሕበራትን ማደራጀት፣ የመሬት ድልድሉን መርዳት ሲሆን ሌላው በመካከል የተፈጠረው እርዮታለማዊ ልዩነቶችን በውይይት ማጥበብ ብሎም ትክክለኛውን አላማ መከተል ነበር።በሰኔ ወር 1967 ዓም ጀምሮ ቀን ከገበሬው ጋር ሲሰሩ ይውሉና ምሽቱን በሕዝባዊ መንግስትና በዴሞክራሲ ጥያቄወች ዙሪያ ውይይቶች ጦፈው ያመሹ ጀመር። ለነዚህ ውይይቶች አራጋቢና ፋና ወጊ ሆነው የወጡት በጊዜው በሕቡ ይታተሙ የነበሩ ጋዜጦች ሲሆኑ በይፋ ደግሞ የጎሕ መጽሄት አቢይ ሚና ነበራቸው። በሕቡ የሚታተሙት አቢዮታዊ ወጣት፣ ዴሞክራሲያና፣ የሰፊው ሕዝብ ድምጽ ቅድሚያ ቦታ ሲኖራቸው ሌሎችም አያሌ በራሪ ወረቀቶችም ነበሩ።

በመስከረም 1968 ዓም ጀምሮ የአዲስ ዘመን እለታዊ ጋዜጣ አዲስ መድረክ ከፈተ። መድረኩም አቢዮታዊ ብሎ ሰየመው። ይህ ጊዜ በኢትዮጵያ የስነጽሁፍና የመናገር መብት ታሪክ ምንም እንኳን ለስድስት ወራት ያክል የቆየ ቢሆንም ሰፊ አበርክቶ አድርጎ አልፏል ብል ማጋነን አይሆንብኝም። በዚህ መድረክ የነ ሁዴ ወንዴሳን፣ አማቹ ማሆጋኖንና የዚያ ትውልድ ታጋይ መሪወችን ክርክር ለማንበብ ብሎም ድጋፍና የተቃውሞ አስተያየቶችን የማስተላለፍ አጋጣሚን ፈጥሮ ነበር።

ዘማቹ በየምሽቱ በሚያደርገው ውይይት የዚህን መድረክ የቀን ተቀን ጽሁፍ ተከታትሎ መተቸት አንዱ ተግባር ሆነ። በ1968 የመጀመሪያ ወራት ሁሉም ባይሆን አብዛኛው ወጣት ዘማች ወደ አንድ በኩል አጋደለ። ከመስከረም 8 እስከ መስከረም 11 ቀን የኢትዮጵያ ሰራተኞች ማሕበር ባደረገው ስብሰባ መሰረታዊ በሆኑ የመብት ጥያቄወች ላይ ውይይት አድርጎ ውሳኔ አሳለፈ። ይህን ስብሰባ ብዙሐኑ ዘማች ተወያይቶ ደገፈ። ሆኖም ከጊዜ ወደጊዜ እርዮታለማዊ ልዩነቶች መፈጠራቸው፤ ትቂቶች ወደአንድ አቅጣጫ ሲሄዱ ብዙሐኑ ዘማች ተማሪ የሕዝብ ጥያቄወችን መደገፍ ብሎም ማቀንቀን ጀመረ። የኢትዮጵያ ሰራተኞችን ማህበር አቋሞች ብዙሐኑ ሙሉ ለሙሉ ደግፎ ሲነሳ ትቂቶች የሰፊው ሕዝብ ድምጽ የሚባለውን ጋዜጣ ተከታዮች ተቃወሙት። በአዲስ ዘመን ጋዜጣ በአብዮት መድረክ የተጀመረው ክርክር በጠዋቱ የኢትዮዝጵያ ሬዲዮ ፕሮግራም ይተላለፍ ስለነበር። በገጠሪቱ ኢትዮጵያ የተበተነው ዘማች ያለማሳለስ ይከታተለው ስለነበር በምሽት ለውይይት ያቀርበዋል። የዴሞክራሲን ጥያቄ አስመልክቶ ብዙሐኑ ዘማች ያለገደብ አሁኑን ይሰጥ ሲል፤ ትቂቶቹ በገደብ አሉ። ጊዜአዊ ሕዝባዊ መንግስ አሁኑኑ ሲል ብዙሐኑ ትቂቶቹ ወታደራዊ መንግስት ጊዜአዊ ስለሆነ ይቀጥል ብለው ተነሱ። በነዚህ ሁለት አቢይ መፈክሮች የተለያየው ወጣት ከቤቱ ሲወጣና ወደዘመቻ ሲሄድ መልካም የነበር ግንኙነቱ ወደሸካራነት ተቀየረ። የሕዝባዊ መንግስትንና የዴሞክራሲን ጥያቄ ያነሱ የዚያ (የየካቲቱ አብዮት) ትውልድ ወጣቶች ጥያቄአቸው ዛሬም በዚያች ምድር ያልተመለሰና፤ አሁንም በተመሳሳይ መልኩ ግፍና ጭቆና የቀጠለ ሲሆን። በአንጻሩ ዴሞክራሲ በገደብ ያሉትና ወታደራዊ መንግስት አብዮታዊ ነው ይቀጥል ያሉት በባንዳነት ተፈረጁ። በዘመቻ ጣቢያወች አብረው የዘመቱ ጓደኞቻቸውን ወደከተማ ከተመለሱ በኋላ አሳሰሩ። አስገረፉ። አስገደሉ። ዛሬም እንደትናንቱ ወያኔ ጠባብ ብሔርተኛ ነው፣ አድላዊ፣ ክልልተኛና፣ ዘረኛ ነው ሲሉ። ይሁንብን ብለው ከጎኑ የቆሙ ከወያኔ ዘር ሳይሆን ወያኔ በነፍጠኝነት፣ በትምክሕተኝነት ከፈረጃቸውና እንደዘር ጠላት ብሎ ከተነሳባቸው የወጡም እንድያኔው፣ በአድርባይነት ተሰልፈው ስናይ ታሪክን መዘከር፣ ማስታወስ ፈለግን።

3 comments:

  1. I think this bloger is member of EPRP and ought to comment on dallaseotc blog recent 2 articles. If you do not respond quickly, we assuming it is a true statement and there was genocide and a crime against humanity in the African Jangle by your group.

    Alex

    ReplyDelete
  2. 
    

    ReplyDelete
  3. An organization never kneeled to any tyrant, be it the fascist derg or the ethnocentric woyane. It’s always a pride being part of EPRP. To answer your question, I will be back after the dust settled down.

    ReplyDelete