Wednesday, November 10, 2010

ለአገር፣ ለወገን፣ ለሰበአዊ መብት፣ ለእኩልነት፣ ለዴሞክራሲ በኢትዮጵያ ደጋፊወች ሁሉ

በዳላስ ፎርትወርዝ ለሚኖር ኢትዮጵያዊ ወገን የትብብር ጥሪ
የተባበሩ አገር ወዳድ ኢትዮጵያውያን

ላለፉት ሦስት አመታት በዚህ በዳላስ በወያኔ በኩል ተቋማትን ለመንጠቅ፣ ነዋሪውን እርስ በእርስ የማጣላት ስልትና የተቃዋሚው የፖለቲካ ስራ ነው ብለው ለምማሳየት ያደረጉት ጥረት በመጠኑም ቢሆን ሰርቶላቸዋል። በዚህ በዳላስ የምንኖር አገር ወዳዶች ይህን የጠላት የመለያየትና የማዳከም ስልት ሌላው እንዲያውቅ በተከታታይ በኢትዮጵያውያን ድሕረ ገጾች አስነብበናል። ማነው ባለሳምንት እንዲሉ እዚህ ዳላስ ከሶስት አመታት በፊት ጀምሮ የታየው የመከፋፈልና የማዳከም፤ ብሎም ተቋማትን በነሱ ደጋፊወች ስር የማዋልን ዘዴ በአለማቀፍ ደረጃ ለመጠቀም መነሳሳታቸውን፣ ብሎም ኢትዮጵያውያን የተመሳሰለና ተስማምተው እንዳይሰሩ ለማድረግ የጀመሩት በሰሜን አሜሪካ እስፖርት ፌደሬሽን ተመልክተናል። ይህ ማለት ፌደሬሽኑ ሄዷል ለማለት እንዳልሆነና ወያኔወች ገቡበት ሳይሆን፤ ያለመስማማት ሁኔታወች እንዲፈጠሩ አስተዋጸኦ ይኖራቸዋል ለማለት ነው።

በዚህ ባለንበት የዳላስ ከተማ ከዚህ በፊት በእስልምና አማኝ ወንድሞቻችን መካከል በቢላል አባላት መካከል ተፈጥሮ የነበረ የመናቆር ሁኔታ እንደነበር ሆኖ። ወደክርስትና አማንያን በመዞር ትልቁን የቅዱስ ሚካኤል ካቴድራል በሶስት ገጽ ፍርድ ቤት አቅርበው አሁንም ያልተቋጨ ቀነቀጠሮ ላይ ይገኛል።

በእኛ እምነት በዚህ በአካባቢ ለተፈጠረ እርስ በእርሳችን እንድንጋጭ ሰፊ የማጥላላት ዘመቻ እራሱን ሁለት ስም ሰጦ በሚንቀሳቀስ የአገዛዙ ደጋፊወች ማሕበር እንደሆነ ተረድተናል። ይህ ማህበር የተቋቋመው ሕላዊ ዮሴፍ የተባለ የመለስ አሽከር ወደዚህ መጦ በነበረበት ጊዜ ይፋ የሕዝብ ስብሰባ ጠርተው አገር ወዳዱ ወደአዳራሽ በመግባት በሰላም ሕዝብን በተለያየ ድለላ ሰብከን እንመሰርታለን ያሉት ሳይሳካ ሲቀርና፤ አዳራሹ በአገር ወዳዶች ሲሞላ፤ ሕላዊና ሌሎች ሁለት ተከታዮቹ ለቀው በመውጣት የድብቅ ስብሰባ በማድረግ ሁለት ስም ያላቸው ተግባርና አላማቸው አንድ የሆነና በተመሳሳይ ሰወችና በቁጥርም ተመሳሳይ በሆኑ የተመሰረቱ ናቸው። አንደኛውን Dfw consensuses committee ሲባል ሌላው “የአማራ ልማት ማሕበር” ይሉታል። እነዚህ ማሕበራት በህላዊ ዮሴ አማካኝነት የተመሰረቱ ሲሆኑ፤ የነዚህ መሪ አባላት ቤተክርስቲያናችንን ከሰው ፍርድ ቤት እያመላለሱን ነው። በኩራትም የክስ ወጭውን እኛ ነን በገንዘብ የምንረዳ በማለት በሕዝብ ስብስብ ፊት ተናግረዋል።

ዛሬ ይንን ጥሪ ለመጻፍ ያነሳሳን፤ በሰሞኑ ከላይ የጠቀስነው የአገዛዙ ደጋፊወች በበተኑት ወረቀት መሰረት በመጭው ቅዳሜ ኖቬምበር 13 ቀን 2010 እዚህ ዳላስ ስብሰባ በመጥራታቸው ሲሆን። እኛም የዳላስ ነዋሪ የሆን አገር ወዳድ ኢትዮጵያውያን ለመላ ወገናችን በዳላስና ፎርት ወርዝ ለሚገኝ ጥሪያችንን ለማድረስ ነው።

ይህ ያለንበት ሳምንት ወያኔ በምርጫ 97 ተሸንፎ በነበረበትና የአውሮፓና በጠቅላላው የውጭ ታዛቢወች መጭበርበሩን በመሰከሩለት፣ የተቀማው የሕዝብ ድምጽ ይከበር ብለው ሰላማዊ ጥያቄ ባቀረቡ ወገኖቻችን ላይ የአጋዚ ሰራዊት ፋሽስታዊ ጭፍጨፋ ያካሄደበት ሲሆን። ሳምንቱም ለሰማእታት ተሰይሞ በብዙ ከተሞች የተከበረበት ነው። በዚህ በዳላስ ከተማም አገር ወዳድ ወገኖች ተሰብስበን አስበነው ውለናል። የዚህን የሰማእታቱን ቀን ከምንም ያልቆጠሩ የአገዛዙ ተባባሪወች የአምስት አመት የልማትና እድገት ብለው ይህን ስብሰባ ሲጠሩ ስናይ ዳግም እኛን በዳላስ ነዋሪ የሆንን ኢትዮጵያውያንን መስደብና መናቅ እንደሆነ ልንገልጽላችሁ እንወዳለን።

ሌላው ልናሳውቅ የምንወደው ወያኔ ለዘመዶቻችንና ለመላ ኢትዮጵያዊው ወገናችን የነፈገውን በነጻ የመሰብሰብ፣ የመደራጀት መብት እዚህ በነጻው አለም ላለን ከኔ ጋር ቁሙ ቢለን ከክህደት አልፎ ለተመልካች የውጭ ዜጎች የአገራችንን ሁኔታ ለሚረዱ ሳይቀር ትዝብት ላይ የሚጥለን በመሆኑ። ሁሉም አገር ወዳድ ወጦ ማንነታቸውን እንዲነግራቸው። በጭቆና ስር ላለው ሚሊወኖች ወገናችን ትብብሩን እንዲያሳይ እኛም ጥሪ እናቀርባለን።

ዴሞክራሲያዊ ምርጫ ባለበት አገር የምንኖር፣ የዴሞክራሲን፣ የመብትን፣ የፍትህን ለዜጎች እኩል መዳረስን አይተን፣ ዳሰንና እኛም ተጠቃሚ ሆነን እየኖርን። ወገናችን በአናሳ ጠባብ ብሄርተኛ ቡድን መዳፍ እየኖረ፤ ዴሞክራሲ አለ። እድገት አለ ኑና ተሰብሰቡ የሚሉ በነዋይ የታወሩ የጠባቡ ቡድን ተባባሪወችን ወግዱ ልንል ይገባል። ከወገን ጋርም የወንድማማችነት/የእህትማማችነት ትብብርን ልናደርግ፤ በጭቆና ስር የሚኖሩ ወገኖችን በተግባር ከነሱ ጋር መሆናችንን የሚያሳይ ስራ ይጠበቅብናል። ሳይሆን ቀርቶ ያባት ቤት ሲወረር በሚል ፈሊጥ የዚህ ጨቋኝ ቡድንን ጥሪ ተቀብሎ ከጎኑ መቆም በታሪክም አስጠያቂ ነው።

ከምንጊዜውም በከፋ በሚሊዮኖች የሚቆጠር ወገናችን የጎዳና ተዳዳሪ በሆነበት፤ በተመሳሳይ ቁጥር ሕጻናት አሳድአጊ አጠው በየመገዱ በሚያድሩበት አገር መሬትና ቤት እንመራለን ብለው ተስፋ የጣሉ ስጋ ስሱ ኢትዮጵያውያን የአምስት አመት የኢኮኖሚ እቅድ በሚል የወያኔ ቧልት ሊያቧልቱን ይፈልጋሉ። አገር ወገን የሚወድ በዳላስና ፎርት ወርዝ የሚኖር ኢትዮጵያዊ ወገን ለነዚህ አድርባዮች ትምህርት ይሰጣቸው ዘንድ ጥሪያችን ይድረሳችሁ።

ቅዳሜ ኖቬምበር 13 ቀን 2010 ዓ.ም በተጠራው ስብሰባ የወያኔ ደጋፊወችን ሳይሆን የወገን አገር ወዳድ ወገኖችን ጥሪ ተቀብሎ በአንድነት፣ በኢትዮጵያዊ ጨዋነት ለማስተማርና ዳግም ከተማችን የወያኔ የፕሮፓጋንዳ መናኸሪያ እንዳትሆን አንድነታችንን የምናሳይበት ቀን ስለሆነ፤ ሁሉም በአካባቢ ከተሞች በፎርት ወርዝ፣ በእርቪንግ፣ በአርሊንግተን፣ በጋርላንድ፣ በሪቻርድሰንና በፕሌኖ የምትኖሩ ትብብራችሁን ለወገን እንድታሳዩ እናሳስባለን።

ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ!!!

ከአገር ወዳድ ኢትያውያን የተላለፈ ጥሪ

1 comment:

  1. የሰማእታቱን ቀን ከምንም ያልቆጠሩ በጅምላ የአገዛዙ ተባባሪወችሊባሉ የሚችሉ አይመስልም። የዳልስ ሕዝብ በሙሉ የሰማእታቱን ቀን ስላላከበረ።

    የወያኔን ወንበዴያዊ ግፈኝነት ለመታገል ብዙ መንገዶች ቢኖሩም የግለሰቦች ምርጫና መብትን በግል አንድ አንድ ግለ ሰብ እንድንሆን በማድርግ በሚወጥንልን መሆን መሐይምነት በስተቀር ለትግሉ አንዲት እርምጃ አያስኬድም።

    እንደኔ እንድኔ ይልቅ ባዘጋጁት መድረክ ስለ ኢኮኖሚ የምናውቀውን እናስተምራቸው።

    ReplyDelete