Monday, November 1, 2010

Let us all be brave enough to die the death of a martyr, but let no one lust for martyrdom. Gandhi

የሕዳሩ ፍጅት
ከሳᎀኤል ሽፈራው

ጥቅምት 21 ቀን 1998 ዓም ከጠዋቱ 3 ሰአት ሲሆን ትቂት ወጣቶች ወደጎዳና ወጥተው የሕዝብ ድምጽ ይከበር; የኢትዮጵያ ሕዝብ ቅንጅትንና ሕብረትን እንጅ ወያኔ/ኢሕአዴግን አልመረጠም። የዘር አድለኦ ያክትም። መብት፣ እኩልነት፣ ለሕዝብ ። በዴሞክራሲ፣ በሰላም ወጦ የመረጠክው ሕዝብ ድምጽ ይከበር። የሚሉ መፍክሮች ይዘው ይታዩ ነበር። ይህ በመርካቶ ክፍለ ከተማ የተጀመረ የሕዝብ ድምጽ ይከበር ሰላማዊ ተቃውሞ በመላ ሐገሪቱ ተዛምቶ ከክልል አንድ (ትግራይ) በቀር በመላ አገሪቱ የሕዝብ መብትን ለማስከበር፤ የተቀማውን ድምጹን ለማስመለስ ወጣት ተማሪወችና አስተማሪወች፤ የከተማ ነዋሪወች፣ የፋብሪካ ሰራተኞች፣ በመንግስት መስራቤቶች ተቀጥረው የሚሰሩ ሰራተኞች፣ የግል ስራወች ያሏቸው፣ ባለሱቆች፣ አናጺወችና ግንበኞች። በጠቅላላው ምልአተ ሕዝቡ የተሰራበትን በደል። አይኑ እያየ መርጦ እንዳልመረጠ ኮሮጆ ተገልብጦ መወሰዱን አውቆ። አሸባሪው የወያኔ መንግስት ምናልባት እራሱ በደነገገው ሕግ ሊዳኝ ይችል እንደሁ በማለት ለአራት ወራት ከጠበቀ በኋላ በዚህ ቀን በሕዳር 21 1998 በመርካቱ ክፍለ ከተማ በተነሳ ሰላማዊ ሰልፍ አማካኝነት ተቀጣጠለ።

በዚሁ አካባቢ 6 ወጣቶች በአጋዚ ጥይት ተደብድበው ሕይወታቸው አለፈ።፡አዲስ አበባ ተናጠች። ሕዝቡ ገንፍሎ ወጣ። አንዳንድ መሪወች ከቅንጅትም ሆነ ከሕብረት ለቃለመጠይቅ ሲበቁ እኛ የለንበትም አሉ። ሕዝቡ የተቀማውን ዽምጽ ይመለስ አለ እንጅ አመጽ ለማነሳሳት አልተነሳም። ይህን በድንጋጤ የሳቱ መሪወችም ግር እንዳላቸው እና መስጠት የሚገባችውን የአመራር ቦታ ትተው እራሳቸውን ለማዳን ተጣጣሩ። ሆኖም በቀልተኛውና ዘረኛ ወያኔ ማንም ምንም ይበል ያሰበውን ያለመውን የመቶ አመት የቤት ስራ ሳይፈጽም ስልጣኑን ለመልቀቅ ዝግጁ አልነበረም። ትግሉ መሪ ይፍፈልጋል። ሆኖም እንደዚያ ባለች ቀጭን ሰአት አንደ አበበ አረጋይ ወይም እንደ በላይ ዘለቀ አልያም እንደ ግርማቸው ለማና ጸሎተ ሕዝⷃስ እኔ ልሙት አለሁ ተከተለኝ የሚል ጠፋ። ያነን ድንቅ ታሪካዊ አጋጣሚ መጠቅም የሚችል አሞተ ኮስታራ መሪ ከመሐላቸው ቢኖር ኖሮ የተከፈለው መስዋእትነት በበቂ ወያኔን አስወድግዶት ነበር። ያልታደለች አገር ያልታደለ ሕዝብ ከሰሜን የተነሳ አናሳ የዘር ድርጅት ወድሮ ስልጣን ላለመልቀቅ ሕዝቡን ደበደቡ።

ምርጫ 97 ከመጀመሩ ትቂት ቀናት በፊት መለስ ዜናዊና ቡድኑ የአጋዚ ጦር ወደአዲስ አበባ አስገባ። ያጦር በቋንቋም ሆነ በክልል ከአንድ አካባቢ የተሰባሰበ በመሆኑ እንደባእድ በሚያየው ሕዝብ መሐል ገብቶ ከታዘዘው በላይ ሰራ። በአንድ ቀን ጥቅምት 21 ቀን ብቻ 200 ኢትዮጵያውያን በአዲስ አበባ ገደሉ። በደም የሰከረው ጠባብ ቡድን ይህ አልበቃውም 150,000 ኢትዮጵያውያንን አሰረ ከአዲስ አበባ ውጭ ወደአዘጋጃቸው ማጎሪካ ካምፖች፣ ዝዋይ፣ ሸዋ እሮቢት፣ ጉደርና ሌሎችም ካምፖች አጓጓዘ።
ድምጻችን ይከበር በማለት በሰላም የወጡ ሁሉ ከሞት የተረፉ በየማጎሪያው በደረቅ ምላጭ እየተላጡ ታጎሩ።

እንዲህ አይነቱ ግፍና መከራ ለኢትዮጵያ አዲስ አይደለመ። በ1969 ዓም አስታጥቁን አታስጨርሱን በሚል አስመሳይ መፈክር የተጀመረው የነጻ እርምጃ፤ ቀይሽብር ይፋፋም በሚል አዲስ መፈክር ተለውጦ አንድ ትውልድን የመተረና የኢትዮጵያዊነት ጉልበትን አዳክሞ ለገንጣይ አስገንጣይ ሐይሎች አሳልፎ የሰጠን የደም ታሪክ ምን ጊዜም ለትውልድ አስተማሪ ሆኖ ይኖራል።

እንደዚያ አይነቱ ግፍና ፍጅት በተሻለ ባለመተካቱ። የሕዝብ ልጆች ዳግም እንዲሞቱ። በግፍ የተገደሉ ኢትዮጵያውያን እሬሳ ዳግም እንዲሸጥ ሆነ።


ጥቅምት 21 ቀን 1998 ዛሬ መላ ነጻነት አፍቃሪ ወገኖች አስበዋት ይውላሉ። በዚህች ቀን ብቻ በአዲስ አበባ ጎዳናወች 200 ኢትዮጵያውያን ደም ፈሷል። እንደ አለመታደል ሆኖ አንድ የመስዋእትነት ገድል ሳይቋጭ በሌላ ይተካል። ኢትዮጵያ የማያቋርጥ ሰማእታትን የምትወልድ አገር እንድትሆን የተፈረደባት መከረኛ አገር ናት። ጥቅምት 21ን እንዘክራለን። ዝክራችን በጠባብ ብሔርተኛው በወያኔ የተገደሉ ሰማእታትን ነው። ይህ ቡድን እንደወራሪው የጣሊያን ሰራዊት ሁሉ ሕዝብን የኔ ብሎ የማይቆጥር ነው። አገሪቷን እንደወራሪ ባእዳን ሁሉ አገሬ ናት ብሎ ስለማያስብ፤ ሐብቷን ንብረቷን ከባእዳን ጋር ያለሥስት ይካፈላል። መሬቷን በቅናሽ ለባእዳን ይቸበችባል። ከ73 አመታት በፊት የካቲት 12 ቀን 1929 ዓ፤ም አዲስ አበባ በጥቁር ለባሽ የጥሊያን ወታደሮች ተቃጥላ ነበር። በዚያው ቀን ጀምሮ ለሶስት ቀናት የዘለቀው ግድያ የ30,000 ኢትዮጵያውያንን ሕይወት ቀሰፈ። ያዲስ አበባ መንገዶች በደም ጎርፍ ተጥለቀለቁ። የአዲስ አበባ ቤቶች የሳት እራት ሆኑ። ወገኖቻችን የፋሽስት ጥቁር ለባሽ ወታደሮች የኢላማ መለማመጃ ተደረጉ። ከስምንት ወራት በፊት ሐምሌ 22 ቀን 1928 ዓ.ም ታላቁ ሰማዕት ብጹእ አቡነ ጴጥሮስ በፋሽስት ጥይት ተደብድበው ተገደሉ። የኢትዮጵያንና የኢትዮጵያውያን መከራና ግፍ በቀጣይነት፤ ከአንድ ሰማእት ትውልድ ወደሌላ ይሸጋገራል። ዛሬም የዛሬ አምስት አመት በነሽብሬ ደሳለኝና ሌሎች 200 ሰማእታት በአጋዚ የተወሰደው ጭፍጨፋ አልረሳነውም። ወደፊትም እንደ የካቲት 12/1929 እና እንደ መጋቢት 1970  (ቀይሽብር) ሁልጊዜ በቀጣይ ይዘከራል።

No comments:

Post a Comment