Wednesday, September 8, 2010

መልስ ለ-------

የግለሰብን መብት ከማሕበረሰብ ፍላጎት ማጋጨት ወይስ ማደናቆር?
ᎀኤል ሽፈራው/ዳላስ

ከሁሉም አስቀድመን የዚህ ብሎግ ዋና አላማ በመከባበር፣ መወያየት ሲሆን ገንቢ ወቀሳ ለሁሉም ጠቃሚ ነው ብሎ ያምናል። ግን በድጋሜ መከባበር ማለት መለባበስ ስላልሆነ ከሚሰጡ ገንቢ ሐሳቦች ትምሕርት መውሰድ፤ ትችቶች እንደአስፈላጊነታቸው መልክ እንዲይዙ ማድረግ ተገቢ ነው። በአንድ የአካባቢያችን ብሎግ በ 9/05/10 በወጣ መጣጥፍ እንዲህ የሚል ሐይለ ቃል ተጨምሮ ስላየን እኛ እንደሚመስለን ብንተቸው መልካም ውጤት ያመጣል ብለን እናምናለን። ወደዚህ የሚወረወር ካለ ለመማር ዝግጁ ነን። ይህ አባባል ከምር ነውና ለበጣ መስሎ እንዳይታይ ከወዲሁ በአክብሮት እንጠይቃለን። ጸሀፊው እንዲህ ያስነብቡናል።

በቤተክርስቲያናችን የስደት ሲኖዶስን ለማስገባት የሚደረገው ጥድፊያ እየታየ  ሲሆን፤ ባለፈው እንደነገርናችሁ ድቁና ለማግኘት ወደ ኦስተን ተልከው የነበሩትን ሕጻናት ለድቁና መብቃታቸውን በደብዳቤና በስልክ ያረጋገጡት የሚካኤል ካህን ይህንን ሲያደርጉ ምን ማለታቸው እንደሆነ ለናንተ  መንገር አይኖርብንም። መልሱ ለሁላችሁም ግልጽ ነውና። በደብዳቤ  እውቅና  ሰጥቶ እከሌን ሹምልኝ እያሉ እኔ ገለልተኛ ነኝ ማለት ደግሞ  "አጨስኩ እንጂ አልዋጥኩትምየሚለውን  ያለፈ የአሜሪካ ባለስልጣን አባባል ያስታውሰናል። ይህ ቤተክርስቲያን በሬሳችን ላይ እንጂ በሕይወት እያለን ለስደት ሲኖዶስ አይሰጥም ይሉ የነበሩትን አዛውንቶች በሉ መሞቻችሁ ይኸው ተቃረበ ለማለት አንወድም፡ መሞታቸውን አንፈልግምና። ይልቁንስ ድቁና የሚሰጡት የስደቱ ሲኖዶሶች ከሆኑ ልጆቻችንን አንልክም ብለው አቋም የወሰዱትን ቤተሰቦች መረዋ በዚህ አጋጣሚ  ስም ሳይጠራ አድናቆቱን ሊገልጽ ይወዳል።    

ይህ የምንኖርበት አገር ሁለት ተከታታይ ጦርነቶች አድርጎ የገነባው ስርአት ለዘብተኛ ዴሞክራሲ ይባላል። በዚህ ዴሞክራሲ እምነት ዋነኛው የስርአቱ እብርት የግለሰብ ነጻነት ያለምንም መገደብ መከበር ነው። ታዲየ ግለሰቦች ያሻቸውን ሊያምኑ፣ ባሻሸው ሊውሉ ሊያድሩ መብታቸው የተከበረ ነው። ይህ መብት ሊገደብ የሚችለው የግለሰቡ ፍላጎትና ተግባራት ከማህበረሰቡ የጋራ ኤቲክስ ከፍ ሲልም ሕግጋት ጋር መጋጨት ሲጀምር ነው። አጋጣሚ ሆኖ ነገርን ነገር ይወልዳልና በዚህ ባሳለፍነው የኢትዮጵያ ቀን ተፈላልገን የተገናኘን የቆየ ወዳጀ ጋር ስንጨዋወት እንዲህ አወጋኝ። ከቤተሰብ አንዱ የአሜሪካን ቦይ እስካውት (Boyscout) አባል ነበርና ወጣቶቹ ከመሪወች ታዝዘው አሮጌ የአሜሪካን ሰንደቅ አላማወች ሰብስበው የምሽት ካምፕ ለማድረግ ወጡ። በዚያን ቀን ይኸው ወዳጀ ተከትሎ እንደሌሎች ወላጆች ይሄዳል። አንድ ነገር ግን አላደረገም። ከሱ ልጅ በቀር ሁሉም ወጣቶች የታዘዙትን ወይም የተሰጣቸውን የአሜሪካን ሰንደቅ አላማ ተሸክመው ነበር የሄዱት። ቀኑን ጉድጓድ ሲቆፈር ይውልና ማታ ፊስካ ሲነፋ ሁሉም ከየድንኳናቸው ወጥተው በሁለት እረድፍ ይሰለፋሉ። ሙዚቀኞች የሙዚቃ መሳሪያቸውን አውጥተው የአሜሪካንን የሕዝብ መዝሙር ዘምረው እንደጨረሱ በየወጣቶች ተከሻ የነበሩ የተቀዳደዱና ያደፉ የአሜሪካን ሰንደቅ አላማወች ወጥተው በየእጃቸው በስነስራት ይታጠፋሉ። ሁሉም አጥፎ እንደጨረሰ ፊስካ በድጋሜ ይነፋል። ወጣቶቹ የቀኝ እጃቸውን ከግራ ደረት በማሳረፍ ቀጥ ብለው እንደቆሙ የአሜሪካ ሕዝብ መዝሙር እየተዘመረ አሮጌ ሰንደቅ አላማወች በክብር እንደተጠቀለሉ ከተቆፈረው ጉድጓድ ይጨመሩና አፈር ተመልሶ ተደፍኖ ስነስርአቱ አበቃ አለኝ። ይኸው በግራሞት ድርጊቱን ሲከታተል የነበረው ወዳጀ ለመጀመሪያ ጊዜ ያየውን ለማወቅ ስለፈለገ የወጣቶችን መሪ ጠየቀው። ያገኘው መልስ “እነዚህ የተቀዳደዱ ሰንደቅ አላማወች አገልግሎታቸውን ስለጨረሱ መሬት ወድቀው ወይም እንደአልባሌ ጨርቅ መጫወቻ ከሆኑ የአገር ክብር ይቀነሳል። ስለዚህ ያ እንዳይሆን በክብር ልክ እንደሰው ልጆች መቀበር አለባቸው” ብሎ ያጫወተውን አወጋኝ።፡የማላውቀው ነገር ስለሆነ በግራሞት አዳመጥሁ ተማርሁ። በኛም አገር የዛሬውን አያርግና። ሰንደቅ አላማችን ከፍተኛ ክብር ነበራት። ከዘረ ያእቆብ እስከ የኤርትራ ተራሮች አብራ ተንገላታለች።፡አያሌ አርበኞች ተጠቅለው ወድቀውባታል። በጀግንነትም እሷን አስቀድመው ተዋግተውባታል። ሰንደቅ አላማ ሲከበር ሁላችንም መንገዳችንን አቋርጠን ቀጥ ብለን ቆመን ተሰቅሎ ወይም ወርዶ እስኪያልቅ በክብር እንጠብቅ ነበር። ነገርን ነገር ያነሳዋልና። ለምን ባገራችን ጠዋት መስቀልና ምሽት ማውረድ እንዳስፈለገ አንድ አዋቂ ነግሮኝ ነበር።፡እንደተሰቀለ ቢያድር ያገር ጠላት ወይም ባለጌ አውርዶ ያገር ክብርን መጫወቻ እንዳያደርገው ነው ብሎኝ ነበር። ይህ አባባል ከዚህ ካሜሪካኖች የአከባበር ባህል ጋር ተመሳሰለልኝ።

ከላይ ያነሳሁትን መጥቀስ ያስፈለገኝ ይህን ያክል ክብር የሚሰጠውን የጋራ መለያ የሆነውን ሰንደቅ አላማ እንኳን ተበደልን ብለው የወጡ ግለሰቦች መከፋታቸውን ለማሳየት እስከማቃጠል ደርሰው ነበር። በ 1968 እ ኤ አ የአሜሪካን ኮንግረስ የቬትናም ጦርነትን በመቃወም የጦርነቱ ተቃዋሚወች በሴንትራል ፓርክ ኒውዮር ያቃጠሉትን እንዳይደገም ሕግ አወጣ። ሕጉም የአሜሪካንን ሰንደቅ አላማ ማቃጠልን አስመልክቶ፤ ሕጉ ከጸደቀበት ቀን ጀምሮ ሕገወጥ እንዲሆን ነበር። ሆኖም የመናገር፤ የመጻፍ፣ ሰላማዊ ሰልፍ የማረግ ነጻነትን ደጋፊ ክፍል በአሜሪካን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ከሶ። ፍርድ ቤቱ በ 1972 እ ኤ አ ማቃጠል የ free speech  አንድ አካል ነው በማለቱ ሕጉ ተነስቷል። ይህን ያክል ለመዘርዘር የተገደድነው በወዳጀ ብሎግ የተጻፈውን ግለሰቦች የወሰዱትን ልጆቻቸውን ድቁና እንዲያገኙ ያደረጉትን አስመልክቶ ጉዞው ገለልተኛ የሆነውን የእምነት ቦታችንን ወደውጩ ሊወስዱት ነው የሚል የይሆናል ክስን በተመለከተ ሲሆን። ለዚህ ትችት ያበቃን ዋና አላማ። ግለሰቦች የፈለጉትን መምረጥ መብታቸው መሆኑን ለጸሐፊው ለማስገንዘብ ሲሆን። በይሆናል ሰው በማያየውና ባልተደረገ (ቤተክርስቲያኑ ወደውጭ ሲኖዶስ ይሁን ያለ ሳይኖር ማለት ነው) ነገር ላይ መተቸት ነውርነቱን እንዲገነዘቡልን ነው። የእምነት ቤታችን ወደውጩ ሲኖዶስ ይሂድ ያለ የለም። ቢኖር እንኳን የሀሳብ ነጻነት ነውና መከበር አለበት።፡ ጸሐፊውና መሰሎቻቸው አይሆም ማለት መብታቸው ነው። እኛም ጸሐፊውም ይህን የሀሳብ ነጻነት ማክበር የግላችንን መብቶችና አስተሳሰቦች የማክበር ያክል መሆኑን እንዲገነዘቡልን እንፈልጋለን። ሕጻናቱ ጳውሎስ በሾሟቸው ጳጳስ ለምን አልተደቆኑም ከሆነ ክርክሩ። ዱባና ቅል አበቃቀሉ ለየቅል ይባል አይደል።

ሌላው ጸሐፊው ደግመው ደጋግመው የውጩን ሲኖዶስ መቃወም ብቻ አይደለም እስከማውገዝ ተጉዘዋል። ታዲያ በሌላው በኩል ለምን ብሎ የተቃወመ ወይም ትርፍ የተናገረ አለመኖሩን እሳቸውም እኛም እናውቃለንና፤ የግል መብት ስለሆነ ለምን ብለን አልተጨነቅንም። ሆኖም እያሳሰበን ያለውና በእርግጥም እንደመረጃ የቆጠርነው፤ ግለሰቡ ፍርድቤት የሄዱ ወገኖችን ደጋፊ እንደሆኑና እሳቸውም ተሳታፊ መሆናቸው የጋራ የእምነት ቤታችንን ወደ አቡነ ጳውሎስ ለመውሰድ የተዘየደ ነው ብለው በምሬት የሚናገሩ ወገኖችን ለማመን የሚያስችል ግምት ውስጥ ግን አስገብቶናል።

ስለፍቅር የሚሰብኩ ቤተክርስቲያን ለምን ይከሰሳል የሚሉ የስደት ሲኖዶስም ደጋፊ አለውና ስለነሱ ባትናገሩ ጥሩ ነው ብለው የድርጅታቸውን ኦፊሻላዊ የአቋም መግለጫ የሚያስተጋቡ አሁንም ነገሮች በውይይት መፈታት አለባቸው የሚሉ መጣጥፎችንም ተመልክተናል። "በፍርድ ቤት ሰላም አይመጣም ማንም ቢያሸንፍ ሁላችንም ተሸናፊዎች ነን"  ብለን በመረዋ ተከታታይ እትምቶቻችን የምንናገረው ስለነበረ  እንኳን ለዚህ አበቃችሁ  እንኳን እውነታው ተገለጸላችሁ ከማለት በስተቀር አባላችንን ኮረጁት  ብለን አልተናደድንም። 

መደናቆር ወይም ማደናቆር እንዳይሆንብን እንሰጋለን። የምናወራው ሰለቤተክርስቲያን ከሆነ። ቤተክርስቲያን ፍቅርን፣ ሰላምን፣ አንድነትን ነው የምታስተምር። ከኛም የምትጠብቀው ያሰተማረችው ተግባራዊ ይሆን ዘንድ ነው። የጸሀፊው ሽሙጥ አይሉት ቃል አዋቂነት በዚህ አባባላቸው ልንረዳ አልቻልንም። ከላይ ብለን ነበር የሚለው ጽሁፋቸው እርስ በራሱ ይጋጭ ይመስለናል። እየከሰሱ እንወያይ። ፍርድቤት ፋይልና ቀነ ቀጠሮ ተይዞ በሰላም እንጨርሰው የሚለው የኒሁ ወዳጀ አባባል ግራ የሚያጋባ ነው። ነገር አያውቁም እንዳንል እኛንም ለማስተማር የሚበቃ እንዳላቸው አንጠራጠርም፤ (ከምር ነው)። በዚህ አገር አንድ በፍርድቤት የተያዘ ጉዳይ በዳኛ ወይም በጁሪ ከመታየቱና ከመቋጨቱ በፊት ለሚዲያ፣ ለውይይት ወይም በሕዝብ መሀል ለክርክር መቅረብ አንዳይችል በዳኛ Gag Order:- ይተላለፋል። ይህ ማለት ሁለቱ ከሳሽም ሆነ ተከሳሽ ስለጉዳዩ ከፍርድቤት ውጭ ሊነጋገሩበት አይገባም ማለት ይመስለናል። እዚህ ላይ ብዙ ባንልም። ይህ በጣም ቀላል የሆነ በመካከላችን በውይይት ሊፈታ የሚችል (የተደበቀ አጀንዳ ከሌለው) ጉዳይ በመሆኑ፤ ይህን ጽሁፍ አቅራቢወች በኒሁ ጸሐፊ የተጠቀሰውን እንወያይ ብለን ነበር የሚለው የለበጣ ነው የሚል አመለካከት አላቸው። ፍርድቤትና ውይይት በአንድ አይሄዱምና ማለት ነው። አሁንም በፍርድቤት ሰላም አይመጣም ስንል።፡ከሳሽ ቢያሸንፍ ምን ሊያረግ ይፈልጋል የሚለውን በኛ በኩል ልናየው ያልቻልነውን ቢያሳዩን መልካም ነበር። ይህ ጉዳይ የአሜሪካን ጠበቆችን በዚህ በክፉ ቀን ገንዘብ ከመስጠት ያለፈና የኛን የተካሰሱ ገመና አውጥቶ ለባእድ ከማሳየት ያለፈ ፋይዳ አለው ብለን አናምነም። ከሁሉም በላይ በድሀ ገንዘብ ተውጣጥቶ የተሰራን የእምነት ቤት ጥሪት የመቀማት ያክል ከባድ ወንጀል ነው ባይ ነን።

ለምን እነእከሌ ያነን ደገፉ ወይም ለምን ይህን ተቃወሙ የሚለው ትችት ገፋ ሲል የአንባገነንነት እርሾ፤ ዝቅ ካለ እኔ ያለሁት ብቻ ትክክል ከሚለው አስተሳሰብ ተዛማጅ በመሆኑ፡ እኛም ለመተቸት አንገደድም። የፈለገውን የማመን መብት ለሁላችን ክቡር ነው ብለን በጥብቅ እናምናለን። ለምን በአቡነ ጳውሎስ አትሳለሙም ባዮች እነሱን አላወገዝንም በኛ ላይ የጳውሎስን አባታችሁ ይሁኑ ሲሉን ግን እንቃወማለን። በጋራ የእምነት ቤታችን የማይሞከር ሕልም እንለዋለን። ፉከራ አይደለም።፡እንደግለሰብ የማንፈልገውን ሊያስገድዱንና ሊጭኑብን አይችሉም ማለታችን ነው። መብታችን ተደፈረ፣ የአገር፣ የወገን መብት ተረገጠ ብለንም እኮ የልጅነት እድሜያችንን አምቢየው አልገዛም ላንባገነን እንዳልን ጸሐፊውም የዛሬውን አያርግና አንዱ ነበሩ ያውቃሉ። በግፍ የተሰደዱ አባቶችን በግል መደገፍም መብት ነው ባይ ነን። እናንተ ካልደገፋችሁ ወዮ ግን አላልንም። ወደፊትም አንልም።

የድርጅታቸውን መግለጫ የሚያስተጋቡ፣ ነገሮች በውይይት መፈታት አለባቸው የሚሉ  ይህ ጸሐፊው የጨመሩትን መግለጫ ወደጎን እንተውና፣ በይሆናል መነጋገር ፋይዳ ቢስ ስለሆነ ማለት ነው። ችግርን በውይይት እንፍታ የሚለው የተሰመረበትን ቃል ነውርነት ግን ሊያስረዱን አልቻሉም።
የነገ ሰው ይበለን

No comments:

Post a Comment