Saturday, September 18, 2010

Current News From Colombia University

ታሪክ ያረገዘው ቀጣዩ የምእራብ የቂም ዘመቻ
     ሳᎀኤል ሽፈራው/ዳላስ

ዛሬ መስከረም 11 ቀን 2003 ዓ.ም መለስ ዜናዊ የተባለ አይን ያወጣ የጥቁር ዘረኛና አንባገነን በኮሎምቢያ ዩኒቨርስቲ ተጋብዞ ንግግር ያደርጋል። የመለስን የክብር ግብዣ አስመልክቶ (ድንቄም) የኮሎምቢያ ዩኒቨርስቲ በድሕረ ገጹ አጭር የሕይወት ታሪክ የመሰለች ለጥፎ ነበር። ሆኖም ባለፈር እሮብ እለት ከድሕረ ገጹ ተነስቷል። ይህ የግል ታሪክ ከኢትዮጵያ ጋር በማያያዝ የሌለና ያልተሰራ ተግባራትን ለጠባብ ብሔርተኛው አንባገነን መለስ በመስጠት ምእራባውያን በድጋሚ ለዚህች አገር ሕዝብ ያላቸውን አይን ያወጣ ንቃቻ ያሳዩበት ነው። ይህ አጭር የመለሰ ዜናዊ የሕይወት ታሪክ ከኢትዮጵያ ጋር የተያያዘ በመሆኑና። አገር አስገኝጥሎ፣ ሕዝብ ከሕዝብ አጣልቶ፣ በዘርና በቋንቋ ሸንሽኖ አሁንም በጠብመንጃ ሐይል በመግዛት ላይ ያለን አገር አጥፊ፤ ባለማወቅ ሳይሆን ግብዣው ለእልፍ አመታት በባርነት የገዙትን የአፍሪካ ሕዝብ በጥቅል ጥላቻና፣ ንቃቻቸውን ዳግም ለማሳየት ሲሆን። በተለይም ለሦስት እልፍ ከንግስተ ሳባ እስከ ማይጮ ገድል ሰርቶ የቅድመ ስልጣኔን ፊርማ አስጠብቆና ጠብቆ የኖረውን የኢትዮጵያን ሕዝብ ሰጥ ለጥ አርጎ የሚገዛን የሰይጣን ድቃይ፣ አንባገነን አግባብ ነው ብለው ለማሳየት የዘየዱት እንደሆነ መረዳታችን አልቀረም።

ምስጋና ይህን ንቃቻ አውግዘው ከአጥናፍ አጥናፍ የተነሳሱትንና ለኮሎምቢያው ፕሬዚዳንት ሚስተር ቦሊንገር የሳምንት የራስምታት የሆኑት ዜጎች ይድረስልኝና። በዩኒቨርሲቲው አመራር አስተሳሰብ “የመልካም አስተዳደር” ተምሳሌ አድርጎ ለመሳል የተሞከረውን የምእራባውያኑ ምሁራን ደናቁርት ተግባር። ከዚያው ከተቋሙ በወጡ ሙያተኛ ዜጋ ምሁራን ደብዳቤና ነቀፋ፤ ገመናውን ማውጣት ተችሏል።

ዩኒቨርሲቲው ቀድሞውንም ቢሆን የመለስ ስራና ተግባር ጠፍቶት ሳይሆን። ያው የለመደባቸው ትእቢትና፣ ንቃቻ ያሳደጉትን ልጃቸውን አበጀህ ብለው ለቀጣይ ጭቆናና አፈና የሞራል ድጋፍ ለማሳየት እንጅ። በነሱ ጥርስ የገቡትን መልካም አስተዳዳሪወች፤ እንደነ ቻቪዝ አይነቶችን አይደለም እናከብረዋለን በምሚሉት መድረክ፤ ባገራቸው የሕዝብ አደባባዮች እንዲደመጡ ምኞቱም ፍላጎቱም የላቸውም።

በሶስተኛው አለም (እስያ፣ ላቲን አሜሪካና፣ አፍሪካ) ሕዝቦች ሰቆቃ አባሪና ተባባሪ የሆነው ምእራባዊው የቅኝ ገዥ (አሜሪካንን ጨምሮ) ያሰበው ሳይሆንና ሳይሳካ ሲቀር። ወይንም በአደባባይ ወጦ ሲጋለጥ። ስራ ተግባሩን የኔነው ሳይል ተገልብጦ አብሮ አዳማቂና አሳባቂ እንደሆነ ከዚህ ካሳለፍነው የ20ኛ ክፍለ ዘመን የደቡብ አፍሪካና የሮዴሽያ (ዚምባᎄኤ) ሕዝቦች ትግል ለመማር ችለናል። የመሀከለኛው አፍሪካን (ኮንጎ) ከቤልጅየም ነጻ ያወጣትን አርበኛ ፓትሪስ ሉሙምባን በአደባባይ ገድለው። ማንነቱና ምንነቱ ያልታወቀውን የቀን ጅብ ሞቡቱ ሴሲሴኮን ለአመታት በማስቀመጥ፤ ከአውሮፓ የነጭ ቅኝ ግዛት ወደ አፍሪካዊው አራጅ በመቀየር እስከዛሬም ለቀጠለው ፍጅትና መከራ የዚያን መከረኛ ሕዝብ ፍዳ አራዝመዋል።

የመጀመሪያው የጥቁር አፍሪካን አንድነት (የተባበሩት አፍሪካን) ሊመሰርት ከላይ ታች ያለውን ወጣት ምሁር ክዋሜ ንኩሩማሕን በመለመሏቸው ቅጥረኞች አስወግደው። ያነን የባሕር ያክል የሰፋ አላማ እንዲመክን አድርገዋል።
በቀዝቃዛው የአለም ጦርነት የውጊአያ ቀጠናቸውን ከምእራብና ምስራቅ አውሮፓ አውጥተው በአፍሪካ ምድር በማዝመታቸው። የኢትዮጵያንና የጎረቤቷን ሶማሊያ ጦርነት ማግደው በመቶ ሽሆች የሚቆጠሩ ወጣት ዜጎችን አስጠፍተዋል።

በራሳቸው ቢመጣ የማይወዱትን። የመገንጠልና የመገነጣጠል አላማን በኛው አገር እንዲተገበር ከ1960ወች ጀምረው ሌት ከቀን በመስራት። ከኤርትራ ተገንጣዮች ኢሳያስ አፈወርቂን፣ ከኢትዮጵያ ዘረኞች መለስ ዜናዊን ኮትኩተው በማሳደግ። ለተደራጁት ጸረ ኢትዮጵያ ሐይሎች ሕግሐኤ/ሕወሐትን በማስታጠቅ በራስ ታሪክና አገር እንዲዘምቱ ማድረጋቸው፡ የማታ ማታ እውን ሆኖ ሁለቱም በድል አድራጊነት አንዱ አዲስ አበባ ሌላው አስመራ በመሆን የእነሱ በየዋሻው በነበሩበት ጥንተ ታሪክ ስልጡንና ጨዋ የሆነውን ሕዝብ ለያይተው አንዱ ያለምንም ጥሪት ደረቅ መሬት ተረክቦ እንዲዘባነን ሲሆን። ሌላው የ80 ሚሊዮኖችን አገር ያለባሕር በር ዘግቶ እንዲገዛት አድርገዋል። ይህ በሁለቱ ወንድማማችና እህትማማች ሕዝቦች መካከል በእጅ አዙር ያካሄዱት ጦርነት ላለፉት ሶስት መቶ አመታት ያዋረደቻቸውን አገር ጣርና ስቃይ እንዲያዩ ስላደረገ። መልካም ተግባር ብለው ሸልመውና በየአለም አደባባዩ እንዲታይላቸው አስጊጠውታል።

የኮሎምቢያ ዩኒቨርሲቲ የሰሞኑ ዝግጅት የዛሬው ግብዣ፤ ከምንም የፈለቀ ሳይሆን። የቂምና የበቀል ጉድጓድ የሚያንዠቀዥቀው ጅረት ለመሆኑ፤ በአገርና በአለም ዙሪያ ያለው ኢትዮጵያዊ ዜጋ ስለሚያውቅ። ዳግም ውርደት ብሎታል።
                                                 

No comments:

Post a Comment