Saturday, September 25, 2010

History is not melodrama, even if it usually reads like that. Robert Penn Warren

89 በኬንያ ፍርድ ቤት ቀርበው የይመለሱ ፍርድ ተፈረደባቸው
ኤል ሽፈራው/ዳላስ

አገራቸውን ለቀው ለአመታት በስደት ይኖሩ የነበሩ የኢትዮጵያ ስደተኞች ከኬንያ እንዲወጡ ተፈረደባቸው። በተመሳሳይ ዜና 26 የመንን አቋርጠው ወደ ሳውዲት አረብ ሲሰደዱ በየመን ወታደሮች ተይዘው ያለፍርድቤት ትእዛዝ ወዳገራቸው እንዲመለሱ የየመን የድንበርና የኢሚግሬሽን ሚኒስቴር አስታወቀ። ይህን ዜና አዲስ ነው ብለን ሳይሆን የኢትዮጵያውያን መከራ ዛሬ ያለም ዙሪያ የእለት ጉዳይ መሆኑን ለመጠቆም ነው።

ለአለፉት አስር አመታት በአረብ አገሮች የተሻለ ሕይወት ለማግኘት የተሰደዱ ኢትዮጵያውያን ወጣት ሴቶች እየደረሰባቸው ያለው ጭቆና ከልክ ያለፈና ጭካኔ የተሞላበት ነው። አንዳንዶቹ የአካል ጉዳት ከደረሰባቸው በኋላ፤ የመኖሪያ ፈቃዳቸውን ጉዳቱን አድራሽ ቀጣሪወቻቸው በመቀማት መልሰው እስር ቤት እንዲሄዱ ያደርጓቸዋል። ይህ ያገር ውርደት አሁንም እንደቀጠለ መሆኑን የአለም የሰባዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶች በተደጋጋሚ አቅረበዋል።

ዛሬ ከሁሉም ያሳዘነንና ግፉ የእጥፍ ድርብ እንዲሆን ያስገረመን የኬንያ መንግስት በስደተኛ ኢትዮጵያውያን ላይ ያስፈረደው ሕገወጥ ፍርድ ነው።

ኢትዮጵያ ለኬንያም ሆነ ለመላ አፍሪካ አለኝታ በመሆን ለዘመናት በአውሮፓ የቅኝ ግዛት ስር ሲማቅቁ ለነበሩ ሁሉ በቀጥታ በትግላቸው ተሳታፊ በመሆን ለነጻነት ለተደረገው ተጋድሎ በደጀንነት ብሎም በቀጥታ ተሳታፊነት አግዛለች። በተለየም በጆሞ ኬንያታ የተመራው (Mau Mau) የነፃ አውጭ ድርጅት በኢትዮጵያ መንግስትና ሕዝብ የተደረገለት ትብብር ያሁኖቹ ገዥወች ቢረሱት ታሪክ ሊዘነጋው አይችልም። ኬንያታ በእንግሊዝ ፍርድቤት 1953 .. የሰባት አመት ጽኑ እስራት ፍርድ ሲፈረድባቸው በዚያን ጊዜ የነፃዋ አገር መሪና በውጭም ከፍተኛ ዝና የነበራቸው ቀዳማዊ ሐይለስላሴ ወዳጅ ለነበረው የእንግሊዝ መንግስት ቅሬታቸውን ገልጸዋል። በዚያ ብቻ አይደለም የተነሳሳው አመጽ እንዲፋጠን ቁሳዊና ሎጅስቲካዊ ድጋፍ አበርክተዋል። ውጤቱም 1958 .. ኬንያታ ከእስር ተፈተው በአንድ ከተማ ተወስነው ከእንግሊዝ መንግስት ጋር የተደረገውን ድርድር በመሪነት አካሂደዋል። ከነፃነት በኋላ በነፃዋ ኬንያ ሊያገለግል የሚችል ሕገመንግስት በማርቀቅ በግዞት ቤታቸው ተወስነው ስራቸውን ጨርሰዋል። ለዚህ ሁሉ የኢትዮጵያ መንግስት ከጎናቸው መቆም ዋና ሐይል እንደነበር ታሪክ ይዘክረዋል።

ለአፍታ ለዝክረ ታሪክ ይሆነን ዘንድ፤ በሱዳን ደቡብና ሰሜን ሱዳን መካከል ተነስቶ ለእልቂት የተቃረበውን የእርስ በእርስ ጦርነት በማቆም። በናይጀሪያ የብያፍራ አመጽ የመጨረሻ እልባት ያገኝ ዘንድ በመሐል በመግባት፤ በሁለቱም አገሮች የነበረውን የመገንጠል አደጋ በሰላም በመፍታት አንድነታቸውን እንዲጠብቁ መፍትሄ በመስጠት። በአልጀሪያና በሞሮኮ ተነስቶ የነበረውን የድንበር ግጭት ሰላማዊ መፍትሄ እንዲያገኝ በማድረግ። በደቡባዊው አፍሪካ የነበሩት የነፃነት ትግሎች በቀጥታ ተሳታፊነትና በአሰልጣኝነት፤ ኢትዮጵያ ያላበረከተችው ድጋፍ አልነበረም። አፍሪካውያን ነፃ በወጡበት አፍላ አመታት 1958 .. በአክራ ስብሰባ ኢትዮጵያ ነጻ የትምህርት እድል ለወጣት አፍሪካውያን በመስጠት ሰፊ አስተዋጽኦ ተደርጓል። ያሁሉ ተረስቶ አገራችን የባሕር በሯን ስትነጠቅና በሁለት ጎጠኛ ወንድማማቾች አደጋ ሲደርስባት ብሎም ዛሬም ኢትዮጵያውያን በመቶ ሺሆች የስደት ኑሮ ሲባዝኑ፤ አይዟችሁ ብሎ የደረሰላቸው አለመኖር እጅ አመዳፋሽ እንዲሊ ሆኗል። ይባስ ብሎ የናት ጡት ነካሽ እንዲሉ በክፉ ቀን መጠጊአያ ፈልገው የተጠጉ ወገኖቻችንን ኬንያ መልሳ ለወያኔ መንግስ ማስረከቧ (ይህ የመጀመሪያ አይደለም) የሚያሳዝን ድርጊት መሆኑን ልናልፈው አንችልም።

ምንጭ፤

Marina de Regt, Ph.D, Amsterdam School for Social science Research
University of Amsterdam

History 101, Spring 1999, Professor Maiershofer

No comments:

Post a Comment