Tuesday, August 31, 2010

የዳላስ ወጣቶች

እንኳን ድስ ያለን የዳላስ ወጣቶች ስብሰባ ጠርተው ሕዝብ ጋብዘው አነጋገሩ

ሳᎀኤል ሽፈራው/ከዳላስ

በአካባቢያችን አንድ አበይት ጉዳይ ተከናወኑ። ይኸውም የወጣቶች መደራጀት ሲሆን ለረጅም ጊዜ ሲጠበቅ የነበረ በመሆኑ እሰየው እንላለን። ለዚህ የእንኳን ደስ ያላችሁ መልእክት ያበቃን የኩነቱን አበይትነት ከታሪክአዊ አመጣጡ ጀምሮ ስለምናውቅ ነው። ዳግም የዳላስ ወጣቶች እንኳን ደስ ያላችሁ ስንል ያለፈ የወጣቱን አኩሪና አንጸባራቂ ኢትዮጵያዊ የተጋድሎ ታሪክ ስለምናስታውስ ነው።

በኢትዮጵያ የአርበኝነት ገድል በየትውልዱ የተነሱ ወጣቶችና የኢትዮጵያ ሴቶች ለዚያች አገር መቀጠል፣ በነጻነት ኮርታ መኖር፣ ዋነኛ ተዋንያን ነበሩ። ያንን ከዘመን ዘመን የተላለፈ አኩሪ ገድል ስናስታውስ ላለፉት አመታት ያየነው የተፋዘዘ ሁናቴም ሆነ፤ አገርን የሚጠሉ ሐይሎች የአገሪቱ አራጊና ፈጣሪ ሆነው ሲገኙ ለዚያ ያበቃቸው የወጣትና የሴቶች ታሪካዊ ተሳትፎ በመጓደሉ እንደሆነ በመተከዝ እናስታውሰዋለን።

ከታሪክ

የዘመነ መሳፍንት ማብቂያ መባቻ ጀምሮ የካሳ በቋራ መነሳትና ለ20 አመታት በክልል ተከፋፍላ የቆየችን አገር መልሶ አንድ ለማድረግ በተካሄደው የአንድነት ዘመቻ በእድሜ ጎልማሳ የነበሩት ካሳና ዋና ፊታውራሪ ሆነው ያንን ተጋድሎ የተሸከሙት የጦር አበጋዝ ገብርየ፤ በአፍላ የወጣትነት እድሜ ክልል እንደነበሩ ታሪክ ይዘክረናል። ከቴወድሮስ ተከትለው ንግስናውን የወሰዱት ዮሐንስም በዋና የጦር አበጋዝነት ያገለገሏቸው አርበኛው ራስ አሉላም ቢሆን ይኸው ወጣት በሚያሰኘው የእድሜ ክልል እንደነበሩ ታሪክ ያጫውተናል።

ታሪክን ዋቢ አድርገን ይህን የምንደረድር፤ አሉ እንድንባል ወይንም ለድለላ አለያም ሽሙጥ ከጅሎን ሳይሆን የወጣቱ ተሳትፎ እስከየት የዘለቀ እንደሆነ ለማሳየት ነው። ዛሬ ይህን ደስታችንን ስንገልጽም ወጣቶች በዚህ ከቀጠሉ የማይናቅ አስተዋጸኦ ሊያበረክቱ መቻላቸውን ከወዲሁ ለመጠቆምም ነው። ታዲያ በርቱ ተበራቱ ስንል የኢትዮጵያ ወጣት ላለፉት ፳  አመታት ተፋዞ በመቆየቱ ይህ የዳላስ ወጣቶች ጅማሮ ምናልባት አንድ የታሪ ቡቅር ጠንሳሽ ሊሆን ይችላልና ነው።

እኛም በመካከለኛ እድሜ የምንገኝም ኖንነ የሽምግልናውን ቋጥኝ የጀመርነው የወጣት ልጆቻችን መሰባሰብና ለማህበራዊ ወይንም የጋራ ጉዳይ ለመከወን መነሳሳትን ትልቅ እርምጃ ወደፊት በመሆኑ፤ እንድናበረታታ ግድ ይለናል። የወጣቶች ትናንትም ሆነ ዛሬ ለጋራ እንቁም ማለት ወጤታማነቱን ያለፉ ታሪካችን ስላስተማሩን። በድህነት የመጨረሻ ጫፍ ላይ ያለች አገርንና፣ በጭቆና ቀንበር ተቀፍድዶ የተደየነን ሕዝብ የነጻነት ተስፋው መጭውና አዳጊው ትውልድ ነውና በርቱ ተበራቱ በሉልን።

በ1928-33 ብተካሄደው ጠላትን ከአገር የማስወጣት ተጋድሎ አንድ አቢይ ነገር ተፈጸመ። ጊዜው 1930 በበልግ ወራት ነበር። ልጅ በላይ ዘለቀ በጊዜው የ24 አመት ወጣት ሲሆን፣ ምክትል ታናሹ እጅጉ ዘለቀ 22 አመት እንደነበር ይነገራል። ከበታች የሁለቱም ታናሽ በናት የሚገናኛቸው ሽፈራው ገርባው የ19 አመት ወጣት ነበር። እነዚህ ሦስት ወጣት ወንድማማቾች ደብረማርቆስ የነበረውን የጠላት ጦር ይከባሉ። ወጣቱ የጋሜወች መሪ የነበረው ሽፈራው የሱን መሰል ወጣት ጦር ይዞ ስለነበር። ሁለቱ ታናናሽ ወንድሞቹን ይዞ ትልቅ ሐይል ይያዘውን የጠላት ጦር የገጠመው ልጅ በላይ ዘለቀ በእኩለ ቀን ድል መቶ የጠላትን ጦር አሸብሮና የሚችለውን መሳሪያ እስከ ባንዳው ማርኮ ብቸና ገባ። ዜናው በአውሮፓ ጋዜጦች በሰፊው መወራቱ ያሳፈረው ጥሊያን። ደካማ እናታቸውንና የበላይን ሚስት ከመኖሪያ ቤታቸው በባንዳ አስከብቦ ይዞ ወደሮማ ላካቸው። እኒህ ሁለት እናትና ባለቤቱ በኋላ ሊመለሱ ችለዋል።

በምእራብ ሸዋ በቀለ ወያና፣ በገረሱ ዱኪ መሪነት ጠላት በአምስት አመት ዘመን እፎይታ ሳያገኝ እንገብግበው እንዳባረሩት ሌላ ታሪክ አስተምሮናል። እነዚህ ሁለት ወጣት አርበኞች ከጦርነቱ በፊት በመሪነት ሊታወቁ ቀርቶ፤ መኖራቸውን ከፈጣሪና ከቤተሰብ ውጭ የሚያውቅ አልነበረም።

ስለወጣቱ ስናወሳ ምንግዜም በአይነቱና ለሕዝብ ብሎ በመነሳት ብሎም መስዋ’እትነት በመክፈል ለታሪክ አሻራውን የለገሰው የየካቲት አቢዮታዊ የኢትዮጵያን ወጣት ሳናወሳ ግን ልናልፍ ይቸግረናል። ዛሬ ወጣቶ በዳላስ ስብሰባ ጠሩን ስንሰማ የነ ቲቶ ሕሩይን፣ የነሱራፌል የካባን፤ የነ ሳᎀኤል ሽፈራውን። ብሎም ከፍ ከፍ ያሉትን ወጣት ምሁራን ገድል፤ የነ ተስፋየ ደበሳይን፤ ግርማቸው ለማ፤ ዮሐንስ ብርሐኔ እና አያሌ ሰማእታት ወጣቶችን ገድል ዘከረን። ይህ የዛሬ የዳላስ ወጣቶች እራስን ማደራጀት በእጅጉ አስደስቶናል። አይዟችሁ፣ በርቱ ተመንደጉም እንላለን። ልናሳስባቸውም የምንፈልገው ቁጥረ ብዙ የሆኑ እዚህ ተወልደው ያደጉ ብዙ ወጣት ምሁራን እየወጡልን ስለሆነ፤ ይህን ተስፋ በማየት መጭው ዘመን የተነቃቃ እንደሚሆን አልተጠራጠርንም። ወጣቶችም አቻ ወንድሞቻቸውን ከጎናቸው ያሰልፉ ዘንድ እኛ ከወጣት እድሜ ክልል ያለፍን ሁሉ ልንተባበር ይገባል እንላለን።

ዛሬ የዳላስ ወጣቶች እንዳለፉት ጀግኖች በር ከፋች ናቸው። በር ከፋች ስንል አዲስ ብስራትን የመደራጀት ዜናን ስላሳዩን ለማለት ነው። ለአመታት የወጣቱ ተሳትፎ የቀዘቀዘውን ያክል፤ይህ አንድ ምእራፍ ከፋች እንደሚሆን አንጠራጠርም። በድጋሜ በርቱ ተበራቱ በማለት በሚቀጥለው ዜና እስክንገናኝ ቸር ይግጠመን



Friday, August 27, 2010

የቅራኔ አያያዝና አፈታት መላወች

መነጋገር ወይስ መነታረክ፧
ᎀኤል ሽፈራው/ከዳላስ


የሐሳብ ልዩነት ወይም አለመስማማት ከቤተሰብ፣ ጀምሮ እስከ ሕብረተሰብ ያለ ኩነት ነው። በእርግጥም ሁሉም ሰው አንድ አይነት አስተሳሰብ ሊኖረው አይችልም። በመሆኑም የሰው ልጅ የቀን ተቀን ግንኙነት ሁሉ የመቻቻል፣ ወይም ሰጦ የመቀበል ተውኔት ነው ይባላል። ልዩነቶች በሁለት ዋና ክፍሎች ይመደባሉ። ቀላል በውይይት የሚፈቱና ከባድ በድርድር አለያም በሐይል የሚፈቱ ተብለው ማለት ነው። አመጽን በሁለት ይከፍሉታል ሰላማዊና በሐይል የተደገፈ በማለት። ሆኖም ማንኛውም ልዩነት በሰላም ሊፈታ እንደሚችል የተለያዩ አዋቂወች ያስተምራሉ። የሰበአዊ መብት ተከራካሪወች ይህን ሐሳብ አይጋሩም።  The two communities have different parents. The human rights community believes that people are bad and need laws because there will always be war, while the conflict resolution community believes people are good and that there is ideal world without war."
Comment by human rights activist at Carnegie Council workshop, July 17, 2001  ባሕል በተለይም ከቅርብ ዘመን ወዲህ ያገኘነው በተቃራኒ ሐሳቦች መካከል ልዩነትን ችሎና አቻችሎ በሰላም ከመፍታት ይልቅ፤ ጽንፈኛ በሆነ ሙሉ በሙሉ እኔ ካላሸነፍሁ በሚል እምነት የሀይለኝነትን ጎዳና እንከተላለን፣ በማያለያየን እንነጣጠላለን። የጋራነት ታላቅ እሴትን ወደጎን ጥለን ላያስተያየን ወደሚችል ከመሬት ተነስተን እንገፋለን። በዚህ በስደት አገራችን ላለፉት ሶስት አስርት አመታት ባገራችን በተንሰራፋው የሰበአዊ መብት ጥሰትና ነፍጥን የያዙ ሐይሎች ሕገወጥ ተግባር ተግባራት የተገፉና ሕይወታቸውን ያተረፉ በመቶ ሽህ የሚቆጠሩ ዜጎች የትውልድ አገርን ለቀው ለመሰደት ተገደዋል። ኢትዮጵያውያን በተሰደዱባቸው  አገሮች ሁሉ በዋልጌነትና አልባሌነት ሳይሆን ሰላማውያን፣ ጠንካራ ሰራተኞችና ተባባሪ በመሆን ይታወቃሉ። ለአብነትም በዚህ በዳላስ ከተማ የነበረ ፍቅር፣ ትብብርና መረዳዳት ለውጭ የሚያስቀና ለኛ ያኮራ እንደነበረ ተረት ሳይሆን የገነባናቸው የጋራ ሐብቶቻችንና መሰባሰቢያወቻችን መመልከቱ በቂ ነው  በዚህ የጋራ ሕሊናዊና ቁሳዊ ሐብትን በማወቅ ወይም ባለማወቅ ወይም በተደበቀ ሌላው በማያውቀው አላማ የጋራ እሴትን አደባባይ አስጥተን ያም ሳይበቃ ለማያውቁን ዳኞች እንዲዳኙን ለፍርድ አቅርበናል። የጋራ ፍቅርንና ትብብርን እንጦሮጦስ ልከን አይሀለሁ፣ እንተያያለን በሚል ፉከራ የቁልቁል ጉዞ ከጀመርን ውልን አድረናል። ከሁሉም ያለንበት ጊዜ አዲስ ተውኔት ሁኖ የሚታየው፤ለአመታት የማይተዋወቁ በምን ምትሐት ተቆራኝተው፣ የጋራ ልሳን ይዘው አደባባይ ሲወጡ፤ ከሚያውቋቸው፤ አብረው ከኖሩ ጓደኞችና ወዳጆቻቸው አይንህ ላፈር ብለው ሲረጋገሙ ስናይ የጠላት ስራ ነው ብንል ስህተት አይሆንብንም ባይሆን ኖሮ ለምንስ ፍርድ ቤት፣ ለምንስ ዶሴ መምዘዝ አስፈለገ፧ ይህን ያዩ በሚኒሊክ ቤተመንግስት ያሉት እረጃጅም እጆች አሉበት ቢሉ ከእውነትነቱ ብዙ የሸሸ አይመስለኝም

እንደኔ እምነት አሉ የተባሉ ችግሮች ለብዙወቻችን ስውር ናቸው። ለትቂቶች ግን ገሀድ ነው መብታችን ተገፏል ይሉናል። ይህን አስመልክቶ እንወያይ እንከራከር የሚሉ ወገኖች ለማቀራረብ ተነሳስተው መልካም ጅማሮ እንደያዙ አይተናል። ሆኖም እንደኔ ግምት ውይይት ቂምን በቀልን ተሸክሞ ሳይሆን ልቦናን ነጻ አድርጎ፣ ከሁሉም በፊት በውይይት ማመንና የሌለ ችግርን ፍርድ ቤት መውሰድ ተጻራሪ መሆናቸውን መቀበል። ከሁለት አንዱ መምረጥ፣ ሁለቱ ግን ባንድ እንደማይሄዱ ማወቅ ይገባል። በዚህ ላይ ምሳሌ ላቅርብ። አንድ ሰውን ከኪሱ ያለውን ነገር የኔነው ብሎ እጁን ጠምዝዞ መንጠቅና፣ ሰውየውን ያ በኪሱ ያለው ነገር የሱ አለመሆኑን በጽሞና ማስረዳት የተለያዩ ነገሮች ናቸው። ወደኛ የጊዜው የተነጋገሩ ግፊት ስንመጣ፣ በአንድ በኩል የተከፈተ ፋይል በፍርድ ቤት የተያዘ ማለት ነው እያለ፤ በሌላ በኩል እንወያይ የሚለው ምስክር ፍለጋ እንደመሄድ የሚቆጠር እንጅ፤ በንጹህ ልቦና የታሰበ አይደለም ባዮች ብዙ ናቸው። በዚያም ተባል በዚህ ይህ ክፉ ጊዜ የጠቀመ ለአሜሪካን ጠበቆች መሆኑን ግን ሁላችንም የምንስማማበት ይመስለኛል።

በአንድ ብሎግ ላይ እሁድ አውገስት ፪፫/፳፲ በቅዱስ ሚካኤል ከጸሎት  በኋላ ስለነበረው የእርዳታ ሙዳይ አስመልክቶ የተወረወረ ትችት አየሁ። ትችት መልካም ነው በኢትዮጵያዊ ጨዋነት ከቀጠለ ያስማማል፤ መልስ ሲሰጠው ፍርድ ቤት የሚያስኬድ ከሆነ ግን ጎጅ የሚሆን ይመስለኛል። ሆኖም ተችው የግለሰቧ የዘር ሀር እግ ቢታወቅ ኖሮ የሚል አባባል ሰንዝረዋል። እንደኔ ከወርቁ የመጡትን መከላከል የተለመደ ቢሆንም። ሌሎችን ትምክህተኞች ብሎ ማጣጣል ሳብ ሲልም ባርባ ጉጉ፣ በበደኖ አይነት ማንገራገርን ማሳየት የለመድነው ቢሆንም፤ እራስ ጠቦና ተጨናንቆ አንድ ሰሞን (አ.ል.ማ) ተመሰረተላችሁ ኑና ተቀላቀሉን የሬዲዮ አዋጅ፤ በአይጋ ፎረም ቅኝት እያደረጉ፤ የቤተክርስቲያኑ የሙዳይ እርዳታ ሌሎችን እንዴት ሲባል መዘዙ አሰኘ፧

Double standard ይሉታል ብዙ ሰወች ችግራችንሚኒሊክ ቤተመንግስት ወራሾች የተዘየደ መላ ነው የሚል እምነት ቢያድድርባቸው ማስተባበል እንዴት ይቻላል፧ ለዚያ እውነትነት ድጋፍ ሰጭ በተግባር የሚታየው በትንሽ በትልቁ በምንተዋወቅ ሰወች ውይይት በሚፈታው ነገር ሁሉ ፍርድ ቤት መሄዱ የድሐውን በባእድ አገር መከራ የሚያየውን አማንያን ጥርጣሬ አጠናክሮታል ባይ ነኝ። አሁንም በመክሰስ በመካሰስ የሚገኝ አሸናፊነት እንደሌለ ታውቆ (ገንዘብ ከማውጣት ባለፈ ማለት ነው) ወንድም ከወንድሙ፣ እህት ከእህቷ ቢነጋገሩ እንዳው ገብስ ነው። መካሪ የጠፋበት ጊዜ ሆነና ጋላቢና ጋሪው የሚገናኙት በሪሞት ኮንትሮል በመሆኑ፣ ጋሪው መንገድ ቢስት መላሹ ከተሰባበረ በኋላ ይሆናል የሚነቃው። ወያኔ የተባለ መጋኛ፤ ሕዝብን በጭቆና ቀንበር አስሮና ለጉሞ መግዛቱ ስላልበቃውና ጥላውን የማያምን አናሳ ድርጅት በባእድ አገር ተበትነው የሚኖሩ ዜጎችን በሪሞት ለመቆጣጠር ፍቱን የሆነ የተፈተነውን የመከፋፈል ልምድ፤ መጋዣ በመግዛት አስማርቷል የሚሉ ወገኖች ብዙ ናቸው። ባለፈው ሰሞን በዋሽንግተን ዲሲ ያየነው ሰልፍን የመሩትና ያዘጋጁት ከወያኔ ትውልድ ቦታ የመጡ ሳይሆኑ፤ እበላባዮች የቆሸሸ ታሪክ ተሸካሚወች እንደ ብርሐኑ ዳምጤ (አባ መላ) የመሳሰሉ ግለሰቦች ነበሩ። እንደሚታወቀው ግለሰቡከፍተኛ ቀበሌ ፩፯ አዲስ አበባ፤ ከሰላሳ አመት በፊት የኖሩ ማንና ምን እንደሰራ ያውቃሉ። አብሮ ቃልኪዳን ገብቶ የተጓደናቸውን ወንድሞቹን አጋልጦ እራሱ ገራፊና አናዛዥ ሆኖ ፫፪ ያህሉን በቀይ ሽብር ካስመተረ በኋላ በጊዜው በነበረው መንግስት የትንምህርት እድል  scholarship እድል ተሰጦት ከዚአያም ተመልሶ በከፍተኛ ስልጣን እንደቆየ ይታወቃል። በተመሳሳይ ዛሬ የምናየው ባገርም ሆነ በውጭ፤ ደጅ የሚጠኑ ወገኖች የሚሰሩት ስራ ከዋነኞቹ በልጦ መታየቱ ባያስገርመን አስደምሞናል። ለነገሩ ውሻ በቀደደው ጅብ ይገባል ነውና እንበለው የሚለውን ትተን በክፉ በደግ አብረን የኖርን ነንና ፍርድ ቤት መመላለስ የጋራ ሕይወታችንና አብሮነታችንን በእጅጉ ስለጎዳ አሁኑኑ ማቆም ይገባል ብለን ለድሮው ፍቅራችን ብንነሳ መልካም ነው። አንዳንዶቻችን ክቡር የሆነውን የፈጣሪን ቃል ባወራንበት የሰው ስም እየጠራን በጭቃ እየጎተትን ስናማትብ ሳይ፤ ምን ማለት እንደሆነ ግራ ይገባኛል። ሌሎቻችን የሱን ቃል ጠርተን እሱነቱን ፍርድ ቤት ስናቆመው ሳይም ወስጠ ሚስጥሩን ለመረዳት ተስኖኛል።
ለሁሉም ልባችንን አራርቶ በሌለ ነገር መባላቱን ትተን፤ ከጥላቻ ፍቅር በላጭ መሆኑን ተረድተን እንመለስ እላለሁ።

በኛ የቅርብ ታሪክ መቸቻል፣ ቅራኔን በውይይት መፍታት፣ ወይንም ባለመስማማት ተስማምቶ ነገርን ለተሻለ ጊዜ ማስተላለፍ እንደነውር የታየበት ጊዜ ሆኗል። ታላቅን ማክበር፣ ጓደኛን እንደራስ መመልከት፣ ለጎረቤትና ለማሕበርተኛ ፍቅርን መለገስ የፋራ ነው የሚያሰኝ ጊዜ ላይ ደርሰናል። አልፎ ተርፎ ከመሬት ተነስቶ ሰውን ማዋረድ እንደትልቅ ሙያ የታየበት አየ ጎበዝ ያሰኘበት ዘመን ላይ ነን።

አንድ ወዳጀ በአንድ ብሎግ እንደጻፉት። ለአንድ ቀን በሄዱበት ቤተክርስቲያን ለመምህሩ አመል አውጠው። ለምእመናኑ ገና በልባቸው እንዲህ ይሉ ይሆናል ብየ ነበር ብለው ሲፈጸሙ በማየቴ በትልቅ የምጠብቃቸውን አውርጀ ባላያቸውም፤ ነገሩ ማሳዘኑን ግን ልቦናየ ሊክድልኝ አልተቻለውም። ትናንሽ ነገርን እየያዝን በዚያ ከዳከርነ፤ ፍሬን (ልጓም) በሌለው አውቶሞቢል እንደተቀመጥን ልንቆጥር ይገባናል። ለሁሉም ነገር መፍትሄው ፍርድቤት ብቻ ለማለት ያበቃንም ይኸው ከልክ ያለፈ ጸጉር ስንጠቃና፣ ሥስ ልቦና ሳይሆን አይቀርም። እንደኔ መድሐኒቱ በመካከል ፍቅር መፍጠር እንጅ መወነጃጀሉ ነው ብየ ስለማላምን። በትንሽ በትልቅ፤ በረባ፣ ባልረባው መቄቂአሙን ገትተን። ፍርድቤት የተባለውን የክስ ዶሴ ዘግተን። በንጹህ ልብ የጋራ ቤትን ለመስራት ብንነሳ መልካም ነው ባይ ነኝ።

ፍርድቤት አሸናፊ እንደሌለውስ እናውቃለን፧ ማን ማንን፧ እንዴትስ ሊረታ ይቻለዋል፧ ቢረታስ ምን ለማድረግ፧

አንዲሁ በሰሞኑ ባየሁት የኒሁ ወዳጀ ትችት የፖለቲካ ድርጅቶች ስደተኛ አባቶችን ደገፉ በማለት ያፌዛሉ። እንዴው ነገርን ነገር ያነሳዋል ነውና አቦይ ጸሐየ ከደህንነት ሹሙ ጋር የዛሬ አንድ አመት በጳውሎስ ስብሰባ የተገኙና መመሪያ የሰጡት። ከዚያስ ጳውሎስን ይቃወማሉ በተባሉ አባቶች የደረሰውን ግፍ እንዴት በዚህ አጭር ወራት ሊረሳ ይቻላልና ነው፧ አሳዛኙ ተውኔትን ከምንም ሳንቆጥር እያለፍን የግፍ ቁና ሰፍረው፣ ድንበርን በእግር አቋርጠው የተሰደዱትን ማናናቅ ለምን አስፈለገ፧ በውጭ ያሉ አባቶችን አለመደገፍ አንድ ነገር ሆኖ እያለ፤ ለዘለፋ ወንም ለምን ተደገፉ ማለት ትቂቶችን ቢያስደስት የሚከፉ መኖራቸውን ማወቅ ተገቢ ነው። የክበር ተከባበር መንፈስ የሚወለደው የራስን ስሜት ለሌላ ሲሉ በመሰብሰብ ይመስለኛል። በሌላ እስከምንገናኝ መልካም ጊዜ ለሁላችን።