Friday, October 21, 2011

እደሚታወቀው የዊኪሊክ ኬብል ረፖርት ከወጣ ወደአንዳመት ሊጠጋው ነው። አሜሪካውያን ዲፕሎማቶች በፊት ለፊት የሚናገሩትና እውነተኛ ሪፖርታቸው የተለያየ መሆኑን ከዚሁ ገመናቸውን ካወጣው ለመረዳት ተችሏል። የአሜሪካንን ጥቅም ለመጠበቅ ሲሉ አንባገነን መንግስታትን ሁሉ በዲፕሎማሲያዊ ለበጣ ያስተናግዳሉ። ባገራችን ኢትዮጵያም የሚሰራው ይህ ነበር። አንዳንድ የመለስ ሕወሐት ደጋፊወች የዘረኛውን መንግስት ቀንደኛ መሪ ችሎታውንና ብቃቱን አስመልክተው ሲደሰኩሩ እንሰማለን። ይህንም አስመልክቶ መለስ ከሃያሉ መንግስት ጋር የጠበቀ ግንኙነት እንደገነባም፣ ለዚያም ተናግሮ የማሳመን ችሎታው እንደሆነ፣ ከሱ የተሻለ ሊኖረን እንደማይችል ሁሉ ይደሰኮርልናል። እንዴውም አንዳንድ ሰወች "እኔ ወያኔን እቃወማለሁ" ይሉንና ፈቅ ሳይሉ የመለስን ዝና ሲተርኩም ይስተዋላል። ያም ሆነ ይህ፣ የዚህን ዘረኛ ሳይኮፓት ገመና በተጋለጸው ኬብል መመልከቱና በተለይም አሜሪካውያኑ ስለግለሰቡና ስለመንግስቱ ምን ያህል እንደሚያውቁ፣ አውቀውም ሊመጣ የሚችለውን እየተነበዩ እንደሆን መረዳት ይቻላል። በእርግጥም አንባገነኖች   በእምነት ከሚጋሯቸው በላይ እበላ ባዮች ግልጋሎት እንደሚሰጧቸው በየጊዜው ታሪክ አሳይቶናል። ነገ ሲመጣ የማይቀረው ውድቀት መለስን ሦስት ጊዜ የሚከዱት እነዚሁ አስመሳዮች እንደሚሆኑ መጠራጠር አይቻልም። ለሁሉም የዊኪሊክን ስለ ኢትዮጵያ የተደረገ ሪፖርታዥ ከታች ባለው ሊንክ ተጠቅመው ይመልከቱ። http://www.cablegatesearch.net/search.php?qo=88