Sunday, December 26, 2010

History is the self-consciousness of humanity,,,,,,,. Droyson

የእድገት በሕብረት የእውቀትና የስራ ዘመቻ
ያትውልድ፤ ከታሪካችን
ከሳᎀኤል ሽፈራው/ዳላስ

ለፍቅር፣ ለብልጽግና፣ ለጸጋና ለእድገት ቀናኢ የሆነ ትውልድ በአገራችን ተነሳ። ያባቶቹን የማይጮ፣ የሽሬ፣ የኤሊባቡር፣ የጎሬ፣ የብቸና፣ የመላ ጎጃም፣ የሜጫ፣ የሸዋና የመላ ጎንደር አርበኝነትን ገድል ካባቶቹ ሲሰማ ያደገው ትውልድ፤ በመንፈስም በስጋም ከነሱ የወሰደውን የጀግንነት ታሪክ በእድገት ለመለወጥ መነሳሳቱ ነበር በኋላ ለዘግናኝ ፍጅት ያውም በወገን እጅ የደረሰበት። የዛሬ ሰላሳ አምስት አመት ታሕሳስ አጋማሽ የእድገት በሕብረት የእውቀትና የትምህርት ዘመቻ ታውጆ በጥር ሁለት ቀን 1967 እ.ኢ.አ የመጀመሪያወቹ ወጣት ተማሪወች ዘመቱ። ለ13 አመታት የታገሉለት የመሬት ላራሹ ሕልምና ሳይማር ያስተማራቸውን አርሷደር ለመቀላቀር የዘመቻ መዝሙራቸውን እያቀነቀኑ ተጓዙ

በእድገት በሕብረት እንዝመት
ወንድና ሴት ሳንል ባንድነት

ዘመቻው አንድ ፊደል የቆጠረ ትውልድን ይዞ የተጓዘ ታሪካዊ ኩነት ነበር። ወጣቶቹ ከቤተሰብ ተለያይተው ወደገጠሪቷ ኢትዮጵያ ሲጓዙ በሀዘን ሳይሆን በደስታና በመንፈሰ ሙሉነት ነበር። አባቶቻቸው በ1928 ዓም ከወራሪ ጠላት ጋር ሲፋለሙ። ገሚሶቹም በአገሪቱ ዱር ገደል እንቢ ለነጻነቴ ብለው በመዋደቃቸው ኢትዮጵያ የተባለችን የጥቁር አገር ክብሯን ዳግም ለመጠበቅ ችለዋል። ታሪካዊውን የአውሮፓ ወራሪ ጠላት ዳግም አሳፍረው መልሰዋል። ይህን በስነ ልቦናቸው ያልለዩት የየካቲት ወጣቶች። የገጠሪቷን ኢትዮጵያ ኑሮ ለመኖር በጉጉት እንጅ በሐዘንና በትካዜ አልነበረም የተጓዙት።

ያትውልድ የምንለው የየካቲቱ ለውጥ ፈላጊ ትውልድ የእድገት በህብረት ዘመቻን በሁለት መንፈስ ነው የተቀበለው። በአንድ በኩል ለዘመናት የተጋደሉለትን የዴሞክራሲና የሕዝባዊ መንግስት ጥያቄ በወታደራዊ መንግስት መነጠቅና ከተማውን ለቀው ቢወጡ ይህ ስልጣኑን ለማደላደል ከወዲያ ወድህ የሚወራጨው ደርግ ጠቅሎ ሊይዝና ምኞታቸውን ሊያደበዝዝ መሆኑ ሲሆን። በሌላ በኩል ለዘመናት የዘመሩለትና የታገሉለት አፈር ገፊውን መቀላቀሉ ለነገ የማይባል አጋጣሚ ሆኖ በመገኘቱ ነው። በዚህ ሁለት አስቸጋሪ ጉዳዮች የተያዘው ወጣት ሆነም ቀረ ዘመቻውን ወደመቀበሉ አመራ። በጥር ሁለት የጀመረው ዘመቻ እስከ ሐምሌ ቀጠለ። 90% የሚሆነው ዘማችም ወደየምድብ ጣቢያው ሔደ።

በየካቲት 25 1967 ዓም አዲሱ የመሬት ላራሹ አዋጅ ወጣ። ምንም እንኳን የተሟላ ባይሆንም፡ ይህን አዋጅ በስራ እንዲተረጎም ያደረገው በዚሁ የእደገት በሕብረት ዘመቻ ላይ የነበረው ወጣት ነበር።

በዚህ አጋጣሚ ስለመሬት ለአራሹ ይሁን ብለው ሰላማዊ ሰልፍ የወጡ ወጣቶች በአገሪቱ የነበረውን የመሬት ስሪት በቅጡ የማያውቁት ብዙወች ነበሩ። ከሰሜን ክፍለ ሀገራት መሬት በእርስት የተያዘበት አካባቢ ተወልደው ያደጉ ሲሆኑ፤ የደቡብ ኢትዮጵያን የጉልተኝነት የመሬት ስሪት አያውቁም። እንዲሁ በደቡብ ኢትዮጵያ ተወልደው ያደጉ ወጣቶች ወደሰሜን ሲዘምቱ እነሱ ተወልደው ካደጉበት የጉልተኝነት ስሪት የተለየ መሆኑ ለነሱም አዲስ ነገገር ነበር። በዚህም ይሁን በዚያ የዚያ የለውጥ ፈላጊ ትውልድ ወጣቶች በአንድና ለአንድ የታገሉ በመሆናቸው ሕዝባቸው የተሻለ ስርአት እንደሚፈልግ፣ ለውጥም መምጣት እንዳለበት በሁሉም የታመነበት ነበር።

ወጣቶቹ ዘመቻ ጣቢያወች ከደረሱ በኋላ፤ ትግሉ መንታ ሆኖ ጠበቃቸው። አንደኛው የገበሬ ማሕበራትን ማደራጀት፣ የመሬት ድልድሉን መርዳት ሲሆን ሌላው በመካከል የተፈጠረው እርዮታለማዊ ልዩነቶችን በውይይት ማጥበብ ብሎም ትክክለኛውን አላማ መከተል ነበር።በሰኔ ወር 1967 ዓም ጀምሮ ቀን ከገበሬው ጋር ሲሰሩ ይውሉና ምሽቱን በሕዝባዊ መንግስትና በዴሞክራሲ ጥያቄወች ዙሪያ ውይይቶች ጦፈው ያመሹ ጀመር። ለነዚህ ውይይቶች አራጋቢና ፋና ወጊ ሆነው የወጡት በጊዜው በሕቡ ይታተሙ የነበሩ ጋዜጦች ሲሆኑ በይፋ ደግሞ የጎሕ መጽሄት አቢይ ሚና ነበራቸው። በሕቡ የሚታተሙት አቢዮታዊ ወጣት፣ ዴሞክራሲያና፣ የሰፊው ሕዝብ ድምጽ ቅድሚያ ቦታ ሲኖራቸው ሌሎችም አያሌ በራሪ ወረቀቶችም ነበሩ።

በመስከረም 1968 ዓም ጀምሮ የአዲስ ዘመን እለታዊ ጋዜጣ አዲስ መድረክ ከፈተ። መድረኩም አቢዮታዊ ብሎ ሰየመው። ይህ ጊዜ በኢትዮጵያ የስነጽሁፍና የመናገር መብት ታሪክ ምንም እንኳን ለስድስት ወራት ያክል የቆየ ቢሆንም ሰፊ አበርክቶ አድርጎ አልፏል ብል ማጋነን አይሆንብኝም። በዚህ መድረክ የነ ሁዴ ወንዴሳን፣ አማቹ ማሆጋኖንና የዚያ ትውልድ ታጋይ መሪወችን ክርክር ለማንበብ ብሎም ድጋፍና የተቃውሞ አስተያየቶችን የማስተላለፍ አጋጣሚን ፈጥሮ ነበር።

ዘማቹ በየምሽቱ በሚያደርገው ውይይት የዚህን መድረክ የቀን ተቀን ጽሁፍ ተከታትሎ መተቸት አንዱ ተግባር ሆነ። በ1968 የመጀመሪያ ወራት ሁሉም ባይሆን አብዛኛው ወጣት ዘማች ወደ አንድ በኩል አጋደለ። ከመስከረም 8 እስከ መስከረም 11 ቀን የኢትዮጵያ ሰራተኞች ማሕበር ባደረገው ስብሰባ መሰረታዊ በሆኑ የመብት ጥያቄወች ላይ ውይይት አድርጎ ውሳኔ አሳለፈ። ይህን ስብሰባ ብዙሐኑ ዘማች ተወያይቶ ደገፈ። ሆኖም ከጊዜ ወደጊዜ እርዮታለማዊ ልዩነቶች መፈጠራቸው፤ ትቂቶች ወደአንድ አቅጣጫ ሲሄዱ ብዙሐኑ ዘማች ተማሪ የሕዝብ ጥያቄወችን መደገፍ ብሎም ማቀንቀን ጀመረ። የኢትዮጵያ ሰራተኞችን ማህበር አቋሞች ብዙሐኑ ሙሉ ለሙሉ ደግፎ ሲነሳ ትቂቶች የሰፊው ሕዝብ ድምጽ የሚባለውን ጋዜጣ ተከታዮች ተቃወሙት። በአዲስ ዘመን ጋዜጣ በአብዮት መድረክ የተጀመረው ክርክር በጠዋቱ የኢትዮዝጵያ ሬዲዮ ፕሮግራም ይተላለፍ ስለነበር። በገጠሪቱ ኢትዮጵያ የተበተነው ዘማች ያለማሳለስ ይከታተለው ስለነበር በምሽት ለውይይት ያቀርበዋል። የዴሞክራሲን ጥያቄ አስመልክቶ ብዙሐኑ ዘማች ያለገደብ አሁኑን ይሰጥ ሲል፤ ትቂቶቹ በገደብ አሉ። ጊዜአዊ ሕዝባዊ መንግስ አሁኑኑ ሲል ብዙሐኑ ትቂቶቹ ወታደራዊ መንግስት ጊዜአዊ ስለሆነ ይቀጥል ብለው ተነሱ። በነዚህ ሁለት አቢይ መፈክሮች የተለያየው ወጣት ከቤቱ ሲወጣና ወደዘመቻ ሲሄድ መልካም የነበር ግንኙነቱ ወደሸካራነት ተቀየረ። የሕዝባዊ መንግስትንና የዴሞክራሲን ጥያቄ ያነሱ የዚያ (የየካቲቱ አብዮት) ትውልድ ወጣቶች ጥያቄአቸው ዛሬም በዚያች ምድር ያልተመለሰና፤ አሁንም በተመሳሳይ መልኩ ግፍና ጭቆና የቀጠለ ሲሆን። በአንጻሩ ዴሞክራሲ በገደብ ያሉትና ወታደራዊ መንግስት አብዮታዊ ነው ይቀጥል ያሉት በባንዳነት ተፈረጁ። በዘመቻ ጣቢያወች አብረው የዘመቱ ጓደኞቻቸውን ወደከተማ ከተመለሱ በኋላ አሳሰሩ። አስገረፉ። አስገደሉ። ዛሬም እንደትናንቱ ወያኔ ጠባብ ብሔርተኛ ነው፣ አድላዊ፣ ክልልተኛና፣ ዘረኛ ነው ሲሉ። ይሁንብን ብለው ከጎኑ የቆሙ ከወያኔ ዘር ሳይሆን ወያኔ በነፍጠኝነት፣ በትምክሕተኝነት ከፈረጃቸውና እንደዘር ጠላት ብሎ ከተነሳባቸው የወጡም እንድያኔው፣ በአድርባይነት ተሰልፈው ስናይ ታሪክን መዘከር፣ ማስታወስ ፈለግን።

Saturday, December 18, 2010

Sorrow is tranquillity remembered in emotion

በመልካም ትህትና ተኮትኩቶ ውብ ድንቅ ኢትዮጵያዊ ባሕል ተላብሶ በቤተክርስቲያናችን ምእመኑን በትህትናው ሲያገለግለን የነበረውን ብርቅ ልጃችን ማቲው ሐይሌን በድንገተኛ አደጋ ተነጠቅን። ወላጅ እናቱ ወ/ሮ መሰረትና አባቱ አቶ ብርሐኑ የደረሰባቸው ከባድ ሐዘን ነው። ጽናቱን ይስጣችሁ። ሐዘናችሁ የሁላችንም ነው። ለሁላችንም ጽናቱን ይስጠን።

Monday, December 6, 2010

After all C++ isn't a perfect match for Java's design aims either,,,. Bjarne Stroustrup

አስቸጋሪው ወር በአዲስ ፍልሚያ ሲተካ
 ሳᎀኤል ሽፈራው/ዳላስ
በዚህ ባሳለፍነው የህዳር ወር ብዙ ነገር በመላ አለም ተመልክተናል። በተለየም አገዛዙ በአገርቤት ያለውን የአፈናና የእመቃ ስርአት በአስተማማኝ መቆጣጠሩን በማረጋገጥ በውጭ የሚኖረውን ስደተኛ ዜጋ ለመግጠም መነሳቱን አመላካች የሆኑ ኩነቶችን ተመልክተናል። ሆነም በእርግጠኝነት ለመናገር ይህ በአገርና በህዝብ የተጠላና የተናቀ ዘረኛ ስርአት የጊዜ ጉዳይ እንጅ ማለፉና መሪወቹም በአገር ማጥፋትና በአገር ክህደት መጠየቃቸው አይቀሬ ነው። ወያኔ/ኢሓዴግ ዘረኛ ስርአት ነው። የሱን የዘረኝነት አባዜ የማይቀበሉትን ሁሉ ማስወገድ እምነቱ ነው። ይህ ደግሞ በውጭ በሚኖረው ዜጋ ሊሞከር የማይችል አጉል ቅዠት ይመስለናል። በዚያ ምትክ አፈላልጎ ያገኘው አዲስ ባይሆንም ተወልዶ ጥርስ የነቀለበትን የዘረኝነትና ጎጠኝነት አስተሳሰብን በቻለው ሁሉ ማዳረስ በመሆኑ። በዚህ እርዮት ለሀያ አመታት ተምረውና ተፈትነው የተዋጣላችው የሚባሉትን በሹመት ሳቢያ ወደውጩ አለም መላክ ነው። የውጭ ጉዳዩን ስዩም መስፍን ወደ ቻይና ሲልክ ግርማ ብሩን ወደዋሽንግተን ካሱ ኢላላን ወደ ኒውዮርክ ሸኝቷል። ይስራ አይስራም የወያኔውን አዲስ የውጊያ ስልት ግን ለማወቅ ብዙ ከባድ አይደለምና፤ ከነዚህ ሹመኞች ጋር ተያይዞ በሙከራ ላይ ያለው በ.አ.ዴ.ን (ብሔረ አማራ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ) በሚል መሪወቹ ኤርትራዊው በረከት ስመኦን፣ የደቡቡ ተፈራ ዋለዋ፤ ኦሮሞኛ ተናጋሪው አዲሱ ለገሰ፣ በትግራይ ሰውነት የሚታወቁት ታደሰ ጥንቅሹ፣ እንወይ ገ/መድሕን፣ ሕላዊ ዮሴፍ እና መሰል ዘረኞች ሲሆኑ በዚህ ድርጅት ስር በውጭ መደራጀት ላይ ያለው አ.ል.ማ ከምንግዜውም በላይ እንቅስቃሴ ላይ ተሰማርቷል። እንግዲህ ይህ ድርጅት ነው አቶ ታየን (አዲስ ለአምባሳደርነት የተሾመ) ጠርቶ በከተማችን ተሞክሮ የነበረውን ስብሰባ የጠራው።

በአስገራሚ ገጽታው በዚህ  ስብሰባ የታዘብነው ቤተክርስቲያን ከሰው በግድ ከምእመን ለመንጠቅ እየሞከሩ ያሎት ግለሰቦች አስተናጋጅና ጋባዥ ሆነው ስናይ አዝነናል። ሌሎችን ፖለቲካ ሰሩ እያሉ እነሱ ከፖለቲካም አልፎ የከፋ የዘር ፖለቲካ ሲሰሩ ስናይ ምን ለማለት እንደፈለጉ ተረድቶናል። ይህን የጠነባ የዘረኛ ስርአት የማይቀበልን መስደብ ማዋረድ ይሁነኝ ብለው የያዙት ስራ ሲሆን። በሰላም ወሎ በሰላም ጸልዮ የሚገባውን ሁሉ ይህን መንግስት ያልተቀበለ አይኑ ላፈር ሲሉን እያየን ነው።

ከዚህ በታች የተጻፈው ስንኝ የተወሰደው ከቤተክርስቲያን ከሳሽ አንዱ ከሆኑት ብሎግ ሲሆን። እንዲህ ይነበባል።

"ቤተክርስቲያን እናት ነችና እናት እንዴት ትከሰሳለች?" እያሉ ለሚጠይቁ ግን ያገሩን ሕግ ካለማወቅ የመጣ ጥያቄ በመሆኑ እናት መከሰስ አይደለም የእናትነት ግዳጇን ካልተወጣች የእናትነት መብቷ ተገፎ ልጆቿን እንደምትነጠቅ መጠቆም እንወዳለን።ቤተክርስቲያንን እናስተዳድራለን ብለው በደል የሚፈጽሙትን ደግሞ ከመክሰስ ሌላ አማራጭ አይኖርም። አማራጭ ቢኖር በጉልበት መፋለም ይሆናል። ያንን ደግሞ እኛ አጥብቀን እንቃወማለን
በዳላስ ቅዱስ ሚካኤል የተጀመረው ወጣት ተረካቢ ትውልድ ለማውጣት እየተካሄደ ያለው እርብርቦሽ ገሐድ ሆኖ እያለ፤ ካፈርሁ አይመልሰኝ በሚያሰኝ አስገማች መጣጥፋቸው ከዚህ በታች ያለውን አስቀምጠዋል። ይህ ሕጻናትን ለማስተማርም ሆነ ያደጉ ወጣት ልጆቻችንን በግብረገብነት ለማውጣት የተጀመረው ልፋት ለኒህ ጸሐፊ እሳቸውና መሰሎቻቸው እስካልመረቁት ድረስ ዋጋ እንደሌለው በቀላል አማርኛ ይጠቅሳሉ።፡ወገን እንዲመለከተው የምንፈልገው፤ ልጆቻችንን ለማስተማርና ለአስተማሪነትም ብቁ የሆነ ምምሁር ለማፈላለግ የወሰደውን ጊዜ፣ ለዚህ የተባረከ አላማ አስፈጻሚ ሆነው የተመደቡ ሰወች፣ ያጠፉትን ጊዜ ሁሉ ከውሃ ጨምረው ከዚህ በታች ያለውን ሲያስነብቡን የግለሰቡ ፍላጎትና አላማ ምን ሊሆን እንደሚችል ማወቅ ከባድ አልሆነልንም። ለዚህ ግልጽ የሆነ ጽሁፋቸው ሳናመሰግን አናልፍም።

አባትና እናት እየበተኑ፡፡ ወላጆችን ከቤተክርስቲያን እያባረሩ። ልጆቹን እያስተማርን ነው ብለው ሲናገሩ አይቀፋቸውምን?የልጆች ነገር አይሆንልኝም የሚሉት አዛውንትስ የወላጆችን  መበተን  በጸጋ  መቀበላቸው ለምን ይሆን? የሚፈሩት ነገርስ ምንድነው? ይህ ባደባባይ የሚነገር ጥያቄ  ሆኖ እየሰማነው ነው።

ማንም የኦርቶዶክስ አማኝ የሆነና በመቅደስ ፊት የቤተክርስቲያኗን እምነትና አምልኮት ለማስተማር በተነሳ አባት ላይ ይህን አይነት ከመስመር የወጣ ትችት ሲመለከት ምን ሊያስብ እንደሚችል መገመት እኒህ ጸሐፊ ምን ያህል ቢሳናቸው ነው ይህን ሊያስነብቡን የደፈሩ?

ባለፈው ሳምንት ካህኑ "ልጆቼንና ባለቤቴን ሸጠህ ትምህርት ቤት አሰራ"  ብለውኛል ተብሎ ከመቅደስ ሲነገር ተገርመን ነበር። ቤተክርስቲያናችን የሰውን ልጅ መሸጥና መለወጥ የማትደግፍ መሆኗን አለማወቅም አስመስሏል።ነገሩ ለአባባል ተብሏል ሊባል ይችል ይሆናል። ነገር ግን የሚነገሩ ቀልዶች የሚያመጡት መዘዝ እንዳላቸው ማሳሰብ ፈልገን ነው። ያንን ማየት መረዳት ደግሞ የማመዛዘን እውቀትን ይጠይቃል።
ይህንንም ወደፍርድ ቤት ለመውሰድ ታስቦ ነው ወይስ ለፌዝ? ለምን ጸሐፊው ሙሉ ቃሉን አልጻፉም? አንድ ሙሉ አረፍተነገር ከእናት ሐሳቡ ተቆርጦና ተነጥቆ ሲቀርብ ልዩ ትርጉም ለመስራት እንደሚችል ፊደል የቆጠረ ሁሉ የሚስተው አይደለም። የዚህን ጽሁፍ አቅራቢም ሆነ “የሰላም አፈላላጊ” የተባሉ ተባባሪወቻቸውን እንዲህ አይነት አጉራ ዘለልና ጥራዝ ነጠቅ ለማንም የሚያኮራ ሳይሆን ሁላችንንም የሚያዋርድ አጸጻፍ ባልሞከሩ ምን ያህል ደግ ነበር?

ጸሐፊው ወረድ ብለው በተቆጣና ተራ በሆነ አነጋገር እንዲህ ይላሉ። የተሰዳቢውን ስም የሰረዘው ይህ ጸሐፊ ተራ ዘለፋ እራስን የሚያዋርድ መሆኑን በጥብቅ ስለሚያምን ነው።

ስካር መንፈስ በየመጠጥ ቤቱ እደባደባለሁ እገላለሁ እያሉ የሚጋበዙት የቅንጅቱ  አቶ ,,,,,, ዛሬ የትጥቅ ትግል ያሉበትን ያልያዙትን ጠመንጃቸውን  ጥለው መስቀል ይዘው ማየታችን ቢገርመንም ይህ ደግሞ ለመልካም ሆኖላቸው ከስካር ቢያድናቸው መልካም በሆነ ነበር። እንደ ቅንጅቱ ማሕተም የቤተክርስቲያኑን ማሕተም ለንግድ ማዋል ይቻላል ብለው በማሰብ ገብተው ከሆነ እንደማይሳካላቸው ካሁኑ ሊነገራቸው ይገባል።ለማንኛውም በዛሬው እለት በመለከት ጦማር ላይ የወጣው የሽማግሌዎችና የአማራጭ አፈላላጊ ኮሚቴ የመጨረሻ ስብሰባ ያረጋገጠልን ነገር ቢኖር ተመራጮቹ ሰላምን እንደማይፈልጉ ቀደም ብለን የተናገርነውን ማረጋገጡ ብቻ ነው። ሽማግሌዎቹ ካሁን በኋላ ያላቸው ምርጫ ቢኖር ብዙሃን ምእመንን ተቀላቅለው በሕግ መፋለሙን መቀጠል ብቻ ይሆናል

ከምር የግል ጥያቄ ነው። በምን የሞራል ሚዛን ነው ለሌሎች መብት ለመከራከር ስል ፍርድ ቤት ሄድሁ ያሉት የዚህ ጸሐፊ የሌላ ግለሰብን መብት ለማዋረድ የተነሳሱት? እንወቃቀስ ከተባለ ከብልግናና አጉራ ዘለል የመንገድ ቋንቋ መውጣት የመጀመሪያ ስራችን በሆነ። ያም ሳይሆን እንዴት የእምነት ቤትን ፍርድ ቤት በዚህ አይነት አነጋገር ለማቆም ተነሳሱ ብለን መጠየቅም መተቸትም እንደአንድ የዚህ ኮሚውኒቲ አባልነታችን ይገባናልና ነው።

Saturday, November 27, 2010

የጸረ ኢትዮጵያ ዘመቻ ዳር ድንበር የት ይሆን?

የኤደን የቤቲ እና የሜላት አማርኛ

ስሙ ካልተጠቀሰ ጸሀፊ የተወሰደ

ለግል /ቤቶች የፈረንጅ ምስል የህልውና ጉዳይ ነው፡፡ በጉልህ የሚታየው የደሞዝ ልዩነትም ለዚህ ጥሩ ማስረጃ ነው፡፡ አንድ በግል /ቤት የሚገኝ ምንም አይነት ዲፕሎማም ሆነ ዲግሪ የሌለው ፈረንጅ የቆዳ ቀለሙ ነጭ በመሆኑ ብቻ ማስተርስ ካለው ኢትዮጵያዊ በአምስት እጥፍ የበለጠ ደሞዝ ያገኛል፡፡ የአንድ ፈረንጅ አማካይ ደሞዝ 5-11 የኢትዮጵያ ብር ይደርሳል፡፡ በአንጻሩ ሁለተኛ ዲግሪና ረዥም የስራ ልምድ ያለው ኢትየጵያዊ መምህር 3 ብር የክፍያ ጣርያው ነው፡፡
በእነዚህ ትምህርት ቤቶች ከፈረንጆች ቀጥሎ ጥሩ ክፍያ የሚያገኙት ህንዶች፣ ጃማይካዎችና ሌሎች የአፍሪካ ዜግነት ያላቸው መምህራን ናቸው፡፡ ሆኖም በስደት ወደ ሶስተኛ አገር ለመሄድ አዲስ አበባ የሚኖሩ አፍሪካውያን ‹‹ሀበሻ›› ደሞዝ ሊቀጠሩ ይችላሉ፡፡
(አሮን ፀሀዬ)
ኤደን ቤቲና ሜላት ገፀ-ባሕርያት አይደሉም፡፡ የገናናው ኀይሌ ገብረ ሥላሴ ሴት ልጆች ናቸው፡፡ በአመዛኙ በእናታቸው ነው የወጡት፡፡ ሲበዛ ቆንጆ ናቸው፡፡ ቀያይ ናቸው፡፡ ፈረንጅ ነው የሚመስሉት፡፡ በዚያ ላይ አማርኛ ይከብዳቸዋል፡፡ እንግሊዝኛ  ይቀናቸዋል፡፡
ከሶስቱ ሴት ልጆቹ መሀል ሁለቱ የመስቀል በዓል ሲከበር አባታቸው ሀዋሳ ላይ ባስገነባው አዲሱ ‹‹`ኀይሌ ሪዞርት›› ተገኝተው ነበር፡፡ ወላጆቻቸው ዓለም እና ኀይሌም ነበሩ፡፡ የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ጋዜጠኛ ተጠጋቸው፡፡ በዓል እንዴት ነው ሲልም ጠየቃቸው፡፡ኀይሌ በዓሉን ከህዝቡ ጋር በማክበሩ ልዩ ስሜት እንደፈጠረበት ተናገረ፡፡
እነ ቤቲ ግን አማርኛ አደነቃቀፋቸው፡፡ ጋዜጠኛው ኀይሌን ‹‹ልጆቹ አማርኛ አይችሉም እንዴ?›› ሲል ጠየቀ፡፡ ኀይሌ በዚያ መልካም ፈገግታው ጥያቄውን ለማስተባበል ሞከረ፡፡ ‹‹…ኸረ እንዲያውም ተረት ይነግሩኸል፣ቅኔም ይዘርፋሉ›› አለ፡፡ ወደ ልጁ ዞሮ፡-
‹‹ተረት ንገሪው እስኪ፤ ግን አጭር ቶሎ የሚያልቅ›› አላት፡፡
ልጅቱ ተጣጣረች፡፡ ምንም አልከሰትልሽ ሲላት ወደ እህቷ ዞረች፡፡ ሀይሌ ትንሽ በሁኔታው የተደናገጠ መሰለ፡፡ እህትየውም ከብዙ ጭንቀት በኋላ አንድ ነገር ተነፈሰች፡፡
‹‹….ዞሮ ዞሮ መግቢያው ጭራሮ!›› አለች፤የሞት ሞቷን፡፡
ሀይሌ የተፈጠረው ሁኔታ በትንሹ ሳይረብሸው አልቀረም፡፡
‹‹…ያው እንግሊዝኛ አስፈላጊ ስለሆነ እንጂ እዚህ ተወልደው አድገው አማርኛን በደንብ ነው የሚያወሩትጎበዝ ናቸው፡፡እንደምታውቀው በዚህ ዘመን እንግሊዝኛ፡፡ያው እንግዲህዌል…›› ኀይሌ በፈገግታው ውስጥ ብዙ ለማስተባበል ሞከረ፡፡
ጋዜጠኛው ቀጠለ፡፡ ኀይሌ የልጆቹን የአማርኛ ብቃት ለማስመስከር ታገለ፡፡ ‹‹መዝሙር በይለት እስኪ›› አላት አንደኛው ልጁን፣ ጥሩ ድምፅ እንዳላትና ኢትዮጵያን አይዶል ብትወዳደር እንደምታሸንፍ ከተናገረ በኋላ፡፡ የደስ ደስ ያላት ልጁ የአማርኛ ወይንስ የእንግሊዝኛ ዘፈን መዝፈን እንዳለባት ጠየቀች፡፡ ኀይሌ አማርኛ ዝፈኚ አላት፡፡ ትንሽ ካሰበች በኋላ ‹‹…..›› ብላ ካጣጣረች በኃላ የሴሌን ዲዮንን ይሁን የማሪያ ኬሪን ለጊዜው የማላስታውሰውን ዘፈን ዘፈነች፡፡ ኀይሌ ፊቱ ቅጭም አለ፡፡
!! አማርኛ!!!
ሞገስ ተፈራ ሁለተኛ ዲግሪውን ከሰራ በኋላ የዩኒቨርሲቲ መምህር ሆነ እንጂ ያለፉትን ዘጠኝ አመታት በግል ትምህርት ቤቶች ነው ያሳለፈው፡፡ ‹‹በእያንዳንዱ ባሳለፍኩት የሥራ ዓመት አማርኛ ሞገሷን እያጣች ነበር›› ይላል የሠራባቸውን ዘመናት በምልሰት እያሰበ፡፡  እንዲህ ይተርካል፡፡
‹‹የትምህርት ቤቶቹን ስም አልጠቅስልህም፡፡ መጀመርያ ተመርቄ እንደወጣሁ ያስተማርኩበት ትምህርት ቤት በጊቢው ውስጥ አማርኛ ከተናገርክ በደሞዝህ ፈረድክ ማለት ነው፡፡ መምህራን በአንድ ዐረፍተ ነገር 15 ብር ይቀጡ ነበር፡፡ ለምሳሌ ረስተህ ‹‹ዳስተሩን አቀብለኝ›› ካልክ 15 ብር ትቀጣለህ፡፡ ‹‹ቾክ ረሳሁ መሰለኝ›› ካልክ ሌላ 15 ብር፡፡ በድምሩ 30 ብር፡፡ ስለዚህ ከመናገር ዝምታን ትመርጣለህ፡፡ አለዚያ ደሞዝህ ተጎማምዶ ይደርስኸል፡፡››
‹‹ተማሪዎች ደግሞ በየሳምንቱ ‹‹language police››የሚባሉሲቪል ተማሪዎች ይመደብባቸዋል፡፡ ከዩኒት ሊደሩ ቢሮ፡፡ ‹‹ላንጉዌጅ ፖሊሶቹ›› ከራሳቸው ከተማሪዎች የተውጣጡ ናቸው፡፡ በእረፍት ሰዓት እየተጫወቱ ድንገት ሲያወሩ አማርኛ የቀላቀሉ ተማሪዎች ስማቸው በእነዚህ የተማሪ ፖሊሶች አማካኝነት ‹‹ዩኒት-ሊደሩ›› ቢሮ ይተላለፋል፡፡ የተለያዩ ቅጣቶች ሲፈፀሙባቸው ትዝ ይለኛል፡፡ ከሁሉም የማይረሳኝ ግን ‹‹I am stupid›› የሚል ባጅ ለጥፈው እንዲዞሩ የሚደረገው የቅጣት አይነት ነው፡፡ በወቅቱ የትምህርት ቤቱ ዳይሬክተር በብሪቲሽ ካውንስል ረዘም ላለ ጊዜ አገልግለው በጡረታ የተገለሉ በሳል ሰው ነበሩ፡፡ ይህ አይነቱ ቅጣት ካልቆመ ሥራ እለቃለሁ እያሉ ሲወተውቱ ትዝ ይለኛል፡፡ የትምህርት ቤቱ ባለቤት እና ዘመዳቸው/ዩኒትሊደሩ/ግን  ‹‹በጀ›› አላሏቸውም፡፡ ሆኖም እርሳቸው ከመልቀቃቸው በፊት እኔ ለቀቅኩ፡፡ በራሴ ምክንያት ነው ታድያ፡፡››
‹‹ከዚያ በኋላ የገባሁበት ትምህርት ቤት በአንዲት ሙስሊም አሜሪካዊት እና /ባሏ ሶማሌ-እንግሊዛዊ ዜግነት ያለው ነው/ የሚተዳደር ሲሆን አብዛኛው የፓርላማ አባላትና መለስተኛ የመንግስት ባለስልጣናት ልጆቻቸውን የሚያስተምሩበት ዝነኛ ትምህርት ቤት ነበር፡፡
የትምህርት ቤቱ አስተዳዳሪ አንቀጥቅጣ ነበር የምትገዛን፡፡ ጥሩ ደሞዝ ብትከፍልም ጥብቅ ዲሲፕሊን ታራምድ ነበር፡፡ በእርሷ ትምህርት ቤት ውስጥ አማርኛ መናገር ክልክል እንደሆነ የሚያሳዩ ማስታወቂያዎች በቅጥር ጊቢዋ በየቦታው በጨርቅ ለጥፋለች፡፡ ገና ስቀጠር በተሰጠኝ የትምህርት ቤቱ ህግ እና ደንብ መግለጫ ላይ ከአማርኛ መምህር ውጭ በክፍል ውስጥ አማርኛ መናገር ያለምንም ማስጠንቀቅያ እንደሚያስባርር የሚገልፅ ዐረፍተ ነገር ተቀምጧል፡፡››
‹‹በእርግጥ ሴትዮዋ በትምህርት ጥራት አትደራደርም፡፡ በጣም ምስጉን ተማሪዎችን አፍርታለች፡፡ ብዙዎቹ ተማሪዎቿ  በእንግሊዝኛ ብቃት እኛ መምህራኖቻቸውን ያስከነዱን ነበር፡፡ በዚህም ትበሳጭብን ነበር፡፡››
‹‹ሌላ የማስታውሳቸው ትምህርት ቤቶች አማርኛ የሚናገሩ ተማሪዎችን ፊታቸውን ወደ ግድግዳ አዙረው እንዲቆሙ ያደረጉ ነበር፡፡ በአንድ ትምህርት ቤት ደግሞ አንድ የአማርኛ ቃል ተሳስቶ ክፍል ውስጥ የተናገረ ተማሪ አንድ ገፅ ሙሉ ‹‹I am sorry›› እያለ እንዲጽፍና እንዲያስፈርመን ይደረግ ነበር፡፡››
‹‹በአጠቃላይ በብዙ ትምህርት ቤቶች አማርኛ ትወገዝ እንደነበር ትዝ ይለኛል፡፡ ወላጆችም ይህ በመደረጉ አድናቆት እንጂ ቅሬታ ሲያቀርቡ ሰምቼ አላውቅም፡፡ በትርፍ ሰዓቴ ልጆቻቸውን አስጠናላቸው የነበሩ ወላጆች ፊደል ያልቆጠሩ ቢሆንም ልጆቻቸው እንግሊዝኛ እያሻሻሉ እንደሆነ ስነግራቸው ይፈነድቁ ነበር፡፡ ሂሳብ እያሻሻሉ ነው ብላቸው ግን እንደዚያ አይፈነድቁም፡፡ ‹‹እሱን ይደርስበታል፣ዋናው እንግሊዝኛ ላይ ይበርታልኝ›› ይሉኻል፡፡
አንዳንዴ ሳስበው ወላጆች ከጎረቤት ጋር ቡና ሲጠጡ በልጆቻቸው እንግሊዝኛ የሚፎካከሩ ይመስለኛል፡፡ ‹‹ ልጄ መቼ አማርኛ ትሰማና፣ እንደው ብታይዋት ጉድኮ ናት፤የፈረንጅ አፍ ነው የሚቀናት›› እያሉ፡፡››
ፈረንጅና ጥቅሙ
አዲስባ ባለፉት አስር አመታት መቶ ሺህ ህፃናትን ወልዳለች፤ መቶ አዳዲስ ሰፈሮችን ፈጥራለች፡፡ መኖርያ ቤቶችን ገንብታለች፡፡ ይህንንም ተከትሎ በታሪኳ ታይቶ በማይታወቅ መልኩ ብዙ የግል /ቤቶች መሽቶ በነጋ ቁጥር በቅለውባታል፡፡ ሰፋ ያለ ጊቢ ያላቸው መኖርያ ቤቶች ድንገት መዋእል ህፃናት ሆነው ይነጋል፡፡ ትምህርት ቤት መክፈት ኪዮስክ ከመክፈት ዘለግ ያለ መሰናዶ የሚደረግለት አይመስልም፡፡
ወላጆች ለአብራክ ክፋዮቻቸው /ቤቱ ሲመርጡ የቅድሚያ መመዘኛቸው /ቤቱ ለእንግሊዝኛ ቋንቋ የሚሰጠው ክብደት ብቻ ነው፡፡ ይህን እውነታ የተገነዘቡ አዳዲስ /ቤቶች መላ አፈጣጠራቸውን ፈረንጅኛ ለማድረግ የማይፈነቅሉት ድንጋይ የለም፡፡ ጥረታቸው የሚጀምረው ለት/ቤት ከሚሰጡት ስያሜ ነው፡፡ በአሁኑ ሰአት በህይወት ካሉ /ቤቶች ምሳሌ ብጠቅስ ሙግቴን ያጠናከርልኝ ይሆናል፡፡
‹‹ጊብሰን አካዳሚ፣ ኩል ኦፍ አሜሪካ አካዳሚ፣  አሜሪካና አካዳሚ ካምብሪጅ አካዳሚ ኦክስፎርድ አካዳሚ ፣ማክሚላን አካዳሚ  ማጂክ ካርፔት አካዳሚ፣ ሂል ሳይድ አካዳሚ፣ ብሪቴይን /ቤት፣  ሜርሲ አካዳሚ፣ ፓራዳይዝ አካዳሚ፣ ሆራይዝን አካዳሚ ሲቲ አካዳሚ ፣ሰንሻይን አካዳሚ፣
/ቤቶቹ ብዙ ተማሪ እንዲመዘገብላቸው በክረምት ወራት በሚያስለፍፏቸው የቴሌቪዥን ማስታወቂያዎች ውስጥ አንድ ፈረንጅ እንዲታይ ያደርጋሉ፡፡‹‹ይህንን አለማድረግ ከፍተኛ ኪሳራን ያስከትላል›› ይላል በተለያዩ የግል /ቤቶች ለዘጠኝ አመት በመምህርነት የሰራው አቶ ሞገስ፡፡  እርሱ እንደሚለው ምስላቸው በቴሊቪዥን እንዲታይ የሚደረጉት ፈረንጆች እንዳንዴ ለማስታወቅያው ብቻ በኪራይ መልክ የሚመጡበት አጋጣሚ አለ፡፡ ወላጆች ልጆቻቸውን ወደ ትምህርት ቤት በሚያመጡበት ሰዓትና ልጆቻቸውን ከትምህርት ቤት በሚወስዱበት ሰአት እነዚህ ፈረንጆች በር ላይ ሆነው የማስተባበር ግዴታ ይጣልባቸዋል፡፡ የዚህ ጽሑፍ አቅራቢ ያነጋገረው አንድ መምህር በአንድ ወቅት ባስተማረበት የግል /ቤት የነበረ ጃማይካዊ ወላጆች በሚገኙበት ሰአት ከፈረንጅ መምህራን ኋላ እንዲሆን በትምህርት ቤቱ አስተዳዳሪዎች ስለተነገረው ቅሬታ ተፈጥሮበት /ቤቱን መልቀቁን ያስታውሳል፡፡
ለግል /ቤቶች የፈረንጅ  ምስል የህልውና ጉዳይ  ነው፡፡ በጉልህ የሚታየው የደሞዝ ልዩነትም ለዚህ ጥሩ ማስረጃ ነው፡፡ አንድ በግል /ቤት የሚገኝ ምንም አይነት ዲፕሎማም ሆነ ዲግሪ የሌለው ፈረንጅ የቆዳ ቀለሙ ነጭ በመሆኑ ብቻ ማስተርስ ካለው ኢትዮጵያዊ በአምስት እጥፍ የበለጠ ደሞዝ ያገኛል፡፡ የአንድ ፈረንጅ አማካይ ደሞዝ 5-11 የኢትዮጵያ ብር ይደርሳል፡፡ በአንጻሩ ሁለተኛ ዲግሪና ረዥም የስራ ልምድ ያለው ኢትየጵያዊ መምህር  3 ብር የክፍያ ጣርያው ነው፡፡
በእነዚህ ትምህርት ቤቶች ከፈረንጆች ቀጥሎ ጥሩ ክፍያ የሚያገኙት ህንዶች፣ ጃማይካዎችና ሌሎች የአፍሪካ ዜግነት ያላቸው መምህራን ናቸው፡፡ ሆኖም በስደት ወደ ሶስተኛ አገር ለመሄድ አዲስ አበባ የሚኖሩ አፍሪካውያን ‹‹ሀበሻ›› ደሞዝ ሊቀጠሩ ይችላሉ፡፡
Amharophobia
በግል /ቤት የሚማሩ ልጆች ጠጠር ያሉ የአማርኛ ቃላትን አይረዱም፡፡ ለምሳሌ ‹‹እርሻ ለአንድ አገር እድገት ይበጃል›› በሚለው አረፍተ ነገር ውስጥ ‹‹ይበጃል›› የሚለው ቃል ግር የሚላቸው 8 ክፍል ተማሪዎች ያጋጥማሉ፡፡ ለአማርኛ ክፍለ ጊዜ የሚሰጠው ክብርና ዋጋም በግል /ቤቶች የወረደ ነው፡፡ ለምሳሌ ፈተና እየተቃረበ ሲመጣ ተማሪዎች በስፖርትና አማርኛ ፔሬዶች ሌሎች ትምህርቶችን እንዲያጠኑ ይደረጋል፡፡
የግል ትምህርት ቤቶች አማርኛ ቋንቋን ትቢያ ለማድረግ የዘየዱት ሌላኛው መንገድ በቅጥር ግቢያቸው አማርኛ መናገር ነውር እንደሆነ ማወጅን ነው፡፡ ከጥቁር ሰሌዳው ጎን በጉልህ ‹‹በአማርኛ መናገር ፈፅሞ የተከለከለ ነው›› የሚል ማስታወቅያ ይሰቅላሉ፡፡ አማርኛ መምህራንም ቢሆን ከክፍላቸው ውጭ በእንግሊዝኛ ብቻ እንዲነጋገሩ ይገደዳሉ፡፡
‹‹ኢትዮጲካሊንክ›› የተሰኘ የሬድዮ ፕሮግራም በአንድ ወቅት በዚሁ ጉዳይ ላይ ባቀረበው ዳሰሳ ‹‹አማርኛ መናገርና ድንጋይ መወርወር ክልክል ነው›› የሚል ማስታወቅያ በአንድ የግል ትምህርት ቤት ተሰቅሎ ማየቱን ዘግቧል፡፡
በግል /ቤቶች መምህራን ተማሪዎችን በፍፁም አካላዊ ቅጣት መቅጣት አይፈቀድላቸውም፡፡ በመሆኑም አማርኛ የሚናገሩ ህፃናት ፊታቸውን ወደ ግድግዳ አዙረው ለተወሰኑ ሰአታት እንዲቆሙ ይደረጋል፡፡ ይህ ከፍተኛው የቅጣት አይነት ነው፡፡ እኔ በተማርኩባቸው የመንግስት /ቤቶች ጆሮ መያዝ፣ እስክሪብቶ በሁለት መሀል ጣቶች ከትቶ መጭመቅ፤ በማስመሪያ ጣቶችን መቀጥቀጥ፣ ኩርኩም እና ወንበር ላይ በሆድ አስተኝቶ በልምጭ መቀመጫን መግረፍ ቀላል ቅጣቶች እንደነበሩ የሚታወስ ነው፡፡
የሀይሌ እንግሊዝኛ
‹‹ዳዲ›› ‹‹ማሚ›› እያሉ ወላጆቻቸውን የማይጠሩ ህፃናት ‹‹ፋራ›› ተደርገው ይታያሉ፡፡ ‹‹እትዮ፣ እቴቴ፣ እታባ፣እማዬ፣ እታብዬ›› የሚሉትን ውብ ቃላት ከልጆች አፍ ለመስማት በከተማ ወጣ ማለትን ይጠይቃል፡፡ በአማርኛው የሚሸማቀቅ ጎንደሬ፤ አማርኛ የሚንተባተብ ጎጃሜ እንደጉድ እየተፈጠረ ነው፡፡
ህፃናት አገርኛ የሆነ መዝናኛ አይቀርብላቸውም፡፡ የኢትዮጵያ ህፃናት በነ‹‹ባርኒ›› በነ ‹‹ሰፓይደርማን›› በነ ‹‹ሲንዴሬላ››እና በነ‹‹ሲምባ›› ፊልሞች አፋቸውን ለመፍታት ይገደዳሉ፡፡ አባባ ተስፋዬ በቴሌቪዥን ተረት መናገር ካቆሙ ስንት ዓመት ሆናቸው? ለነገሩ በእርሳቸው የመጨረሻ የስራ አምታትም ተረቶቻቸው ላይ የሚሳለቁ ልጆች እየተፈጠሩ እንደነበረ ትዝ ይለኛል፡፡ ‹‹ልጆች-የዛሬ አበቦች የነገረ ፍሬዎችቁጭ በሉአትጋፉ…! በሚሉበት ሰአት ‹‹ሪሞት›› የያዙ ብዙ የአዲሲቷ እትዮጵያ ህፃናት “WHAT!! “ ማለት ይጀምራሉ፡፡
የኀይሌ ልጆች ከዚሁ ትውልድ ውስጥ ሊደመሩ ይችሉ ይሆናል፡፡ የኀይሌን ሀገር ወዳድነት በእንግሊዝኛ ብቻ መረዳት ግን የሚከብድ ይመስለኛል፡ አባት ኀይሌ የእንግሊዝኛን ጥቅም በተግባር ያውቃታል፡፡ ልጆቹ እርሱ በቻለበት መንገድ ቋንቋዋን እንዲችሏት የሚሻ አይመስለኝም፡፡ በዚህ የተነሳ ውድ ልጆቹ ኤደን፣ሜሪና ቤቲ አማርኛን እንዲደነቃቀፉ ፈቅዷል፡፡ ለባንዲራው የሚያለቅሰው ኀይሌ እንዲሆን ከፈቀደ ማን ቀረን ታድያ?