ሳᎀኤል ሽፈራው/ዳላስ
መልካም አዲስ አመት ለመላ ኢትዮጵያውያን። ለእስልምና ተከታይ ወገኖች ኢድ ሙባረክ። ይህ አዲስ አመት የመልካም ተስፋ መፍቻ እንዲሆን ለሁሉም ዜጋ ምኞታችን ነው።
መልካም አዲስ አመት ለመላ ኢትዮጵያውያን። ለእስልምና ተከታይ ወገኖች ኢድ ሙባረክ። ይህ አዲስ አመት የመልካም ተስፋ መፍቻ እንዲሆን ለሁሉም ዜጋ ምኞታችን ነው።
ከአመታት በፊት አገሬን ለቅቄ ስወጣ አዲስ ሆኖ ያገኘሁትና ለሁልጊዜ እንድዘጋጅበት ለጽናት የተቀመጥሁበት ጉዳይ ቢኖር የዘመን አቆጣጠርን ነበር። የኛ የዘመን አቆጣጠር ከምእራባውያንም ሆነ ከምስራቅ አገሮች የተለየ ነው።
አንዳንድ ወገኖች ይህን የዘመን አቆጣጠር ከግብጽ የኮፕቲክ ቤተክርስቲያን ጋር ሊያዛምዱት ይሞክራሉ። ሌሎቹ ደግሞ ከአውጉስቶስ ጁሊየስ የዘመን አቆጣጠር ጋር ያዛምዱታል። ይህ የማዛመዱ ዝንባሌ የአገራችንን ጥንታዊ የስልጣኔ ዘመንን ላለመቀበል ነው የሚሉ ሊቃውን አሉ። ሌላው ቀርቶ ለእልፍ አ’እልላፍ አመታት አብረው የኖሩና እራሳቸውን የገነጠሉትም የድንበር ብቻ ሳይሆን በታሪክና በማንነትም ገንጥለዋል። በማኮብኮብ ላይ ያሉትና የራሳቸውን የስልጣኔ ምንጭነት የካዱ ወይንም ያልተቀበሉ በአይነቱ ልዩና ብቁ የሆነውን ፊደላት ላለመቀበል ያድረጉትን አይተናል። የሆነው ሆኖ በዚያች ምድር የተፈጠርን ሁሉ ዛሬ ያዲስ አመት መለወጫ በመሆኑ፤ የሰላም፣ የፍቅር፣ የብልጽግናና የስምምነት አመት ይሆን ዘንድ እንመኛለን። ይህ አዲስ አመት እኛ ብቻ የምናከብረው በመሆኑ። በአይነቱ ልዩ የሆነውን ቀን ለሰጡን የቅድመ ስልጣኔ አባቶች ምስጋና ይድረሳቸው። እኛም ልንኮራበት ይገባል።
ዛሬ ከ2002 ወደ 2003 የተሸጋገርንበት አዲስ አመት ነው። የግብጽ ኮፕቲክ አማንያን ደግሞ 1727 ሆነ ማለት ነው። የግብጽ ኮፕቶች የዘመን ቆጠራ የጀመሩ በክርስቶስ ልደት አያይዘው ሳይሆን 276 አመት ዘግይተው እንደሆነ ይነገራል።
የኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ የተገኘ ነው ሲሉ ሆኖም የግእዝ ስልጣኔ አንድ አካል ነው ባዮችም አሉበት። ግእዛውያኑ እንደመረጃ የሚያቀርቡት። ከቤተክርስቲያን ጋር የተያያዘ ታሪክ ቢሆን ኖሮ ከግብጽ ኮፕቶች የተመሳሰለ የዘመን ቆጠራ ይኖረን ነበር በማለት መረጃ ያቀርባሉ። በሌላ በኩል ኢትዮጵ ከክርስትና በፊት የይሁዳዊ እምነት ተከታይ ስለነበረች የዘመን ቆጠራ ከዘመነ ይሁዳ ጀምሮ የነበር ቅድመ ስልጣኔአችን መሆኑን በተግባር በያመቱ የምናከብረው አዲስ አመት ያስታውሰናል። እንደሚታወቀው መሬት በተፈጠረች በስምንተኛው ሽህ፤ ዳግም ምጣት ይሆናል ተብሎ በኛ ይታመናል። ለዚህም በኢትዮጵያ የዘመን ቆጠራ መሰረት ከክርስቶስ ልደት በፊት የነበርውን ዘመን አመተ አለም (ፍዳ) ስንለው። እስከ ጌታ ልደት 5500 አመተ አለም (ፍዳ) እንደቆጠርን የኛ አቆጣጠር ያስተምራል። በሌላ በኩል ከክርስቶስ ልደት በኋላ ያለውን ዘመን የምህረት ዘመን ስለምንለው፤ አመተ ምህረት ይባላል። በመሆኑም በግእዝ ስልጣኔ የዘመን ቆጠራ መሰረት ዛሬ ከመጀመሪያ ፍጥረት ጀምሮ 7503 ዘመን ሆነ ማለት ነው። በእምነታችን ተመርኩዘን ዛሬ ለስምንተኛው ሽህ 497 አመታት ብቻ ቀርቶታል ማለት ነው።
ምእራባውያንም ሆኑ ምስራቃዊው አለም ቻይናንና ሕንድን ሳይጨምር የዘመን ቆጠራቸው ግሪጎሪያን ይባላል። የግሪጎሪያን ዘመን ቆጠራ ከኛ በ7ና 8 አመታት ሲቀድመን። አንድ አመት 12 ወሮች ወይንም 365.2425 ቀናት ይኖሩታል። በተመሳሳይ የግእዝ ዘመን ቆጠራ 13 ወራት ይሆኑና ጳግሜ ወር ከአራት አመት አንድ ጊዜ ስድስት ቀናት ሲኖራት ቀሪውን ሶስት አመታት አምስት ትሆናለች። በመሆኑ የኛ አዲስ አመታችን መስከረም አንድ ቀን ይጀምራል። ይህ ማለት በግሪጎሪያን አቆጣጠር በ ዘጠነኛው ወር በ11 ቀን ላይ ይውላል ማለት ነው።
ከዶክተር አበራ ሞላ የዘመን ቆጠራ ታሪክ የተወሰደ።
በድጋሚ መልካም አዲስ አመት ወድ ኢትዮጵያውያን።፡በተጨማሪ የእስልምና ተከታው ወገኖች ዛሬ ሁለት አውዳመት በአንድ ቀን ስለሆነላችሁ እንኳን አደረሳችሁ እንላለን።
እንቁጣጣሽ

No comments:
Post a Comment